አትበቀል፤ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና።
ሉቃስ 10:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም መልሶ፥ “እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ሰውነትህ፥ በፍጹም ኀይልህ፥ በፍጹም ዐሳብህ ውደደው፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ ይላል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየውም መልሶ፣ “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህና በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ’ ይላል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም መልሶ፦ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየውም “ሕጉማ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ኀይልህ፥ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤’ እንዲሁም ‘ጐረቤትህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ፤’ ይላል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም መልሶ፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው። |
አትበቀል፤ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና።
በኦሪት እንዲህ ብሎአልና፥ “አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፥ አትመኝ፤” ደግሞ ሌላ ትእዛዝ አለ፤ ነገር ግን የሁሉም ራስ “ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚለው ነው።
ወንድሞች ሆይ፥ እናንተስ ለነጻነት ተጠርታችኋል፤ ነገር ግን በሥጋችሁ ፈቃድ ለነጻነታችሁ ምክንያት አታድርጉላት፤ ለወንድሞቻችሁም በፍቅር ተገዙ።
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ ነው እንጂ፥
በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህን እግዚአብሔርንም በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ እንድትወድድ እግዚአብሔር ልብህን፥ የዘርህንም ልብ ያጠራዋል።
ከእነዚያ ዘመናት በኋላ ለቤተ እስራኤል የምገባው ቃል ይህ ነው፦ ሕጌን በልባቸው አሳድራለሁ፤ በሕሊናቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል ይላል እግዚአብሔር።