ሉቃስ 1:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባርያውን ትሕትና ተመልክቶአልና። እነሆ፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ የባሪያውን መዋረድ ተመልክቷልና። ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ምስጉን ይሉኛል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔን ዝቅተኛይቱን አገልጋይ ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እኔን ዝቅተኛ አገልጋይቱን ተመልክቶአልና፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ የተባረክሽ ነሽ ይሉኛል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ |
አሁንም ዳዊትን ባሪያዬን እንዲህ በለው፦ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰድሁህ፤
ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ የዋሁና ወደ ጸጥተኛው፥ ከቃሌም የተነሣ ወደሚንቀጠቀጥ ሰው ከአልሆነ በቀር ወደ ማን እመለከታለሁ?
መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ፥ “ደስ ያለሽ፥ ጸጋንም የተመላሽ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፤ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው፤ ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ” አላት።
ከዚህም በኋላ ይህን ሲናገር ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን አሰምታ፥ “የተሸከመችህ ማኅፀን ብፅዕት ናት፤ የጠባሃቸው ጡቶችም ብፁዓት ናቸው” አለችው።
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።
ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።