ዘሌዋውያን 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም እጆቹን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ ባረካቸውም፤ የኀጢአቱን፥ የሚቃጠለውንም፥ የደኅንነቱንም መሥዋዕት ከሠዋ በኋላ ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም እጆቹን ወደ ሕዝቡ ዘርግቶ ባረካቸው፤ የኀጢአት መሥዋዕቱን፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረቱን መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም እጆቹን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ ባረካቸውም፤ እርሱም የኃጢአቱንና የሚቃጠለውን የሰላሙንም መሥዋዕት ከሠዋ በኋላ ወረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንም ይህን ሁሉ መሥዋዕት አቅርቦ እንደ ጨረሰ እጆቹን በሕዝቡ ላይ ዘርግቶ ከባረካቸው በኋላ ወረደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም እጆቹን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ ባረካቸውም፤ የኃጢያቱን የሚቃጠለውንም የደኅንነቱንም መሥዋዕት ከሠዋ በኋላ ወረደ። |
የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ለቅድስተ ቅዱሳን የተቀደሰ ይሆን ዘንድ ተመረጠ፤ እርሱና ልጆቹ ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ፊት ያጥኑና ያገለግሉ ነበር፤ በስሙም ለዘለዓለም ይባርኩ ነበር።
ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፥ አድርገውት ነበር፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።
እግዚአብሔርም አስቀድሞ ልጁን አስነሣላችሁ፤ ሁላችሁም ከክፋታችሁ እንድትመለሱ ይባርካችሁ ዘንድ ላከው።”
በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸከም ዘንድ፥ እርሱንም ለማገልገል በእግዚአብሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስሙም ይባርክ ዘንድ እግዚአብሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።
የሌዊ ልጆች ካህናትም ይቀርባሉ፤ በፊቱ እንዲያገለግሉ፥ በስሙም እንዲባርኩ አምላክህ እግዚአብሔር መርጦአቸዋልና፤ በእነርሱም ቃል ክርክር ሁሉ ጕዳትም ሁሉ ይቆማልና፤