“አንተም ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አብዩድንም፥ አልዓዛርንም ኢታምርንም አቅርብ።
ዘሌዋውያን 7:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን በክህነት ያገለግሉት ዘንድ በተቀቡበት ቀን ለእግዚአብሔር ከሆነ ከእሳት ቍርባን የአሮንና የልጆቹ ሕግ ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናት ሆነው እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ በቀረቡ ቀን፣ በእሳት ለእግዚአብሔር ከቀረበው መሥዋዕት ላይ ለአሮንና ለልጆቹ የተመደበላቸው ድርሻ ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታን በክህነት እንዲያገለግሉት እነርሱን ባቀረባቸው ቀን ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም እግዚአብሔር አሮንንና ልጆቹን ካህናት አድርጎ በሾመበት ቀን ለእግዚአብሔር ከቀረበው ከሚቃጠል መሥዋዕት ለካህናት ድርሻ ሆኖ የተለየ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን በክህነት ያገለግሉት ዘንድ ባቀረባቸው ቀን ለእግዚአብሔር ከሆነ ከእሳት ቁርባን የአሮንና የልጆቹ እድል ፈንታ ይህ ነው። |
“አንተም ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አብዩድንም፥ አልዓዛርንም ኢታምርንም አቅርብ።
“እኔንም በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርግላቸው ነገር ይህ ነው፤ ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች ትወስዳለህ።
በመሠዊያውም ላይ ካለው ደም ከቅብዐት ዘይትም ወስደህ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ ከእርሱም ጋር ባሉት በልጆቹና በልብሶቻቸው ላይ ትረጨዋለህ፤ እርሱም ልብሶቹም፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹ፥ ልብሶቻቸውም ይቀደሳሉ።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
ሙሴም ከቅብዐቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ከአለው ከደሙ ወስዶ በአሮንና በልብሱ ላይ ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም፥ የልጆቹንም ልብስ ቀደሰ።
እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።
ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆነኝ ዘንድ፥ በመሠዊያዬም ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣንንም ያጥን ዘንድ፥ ኤፉድንም በፊቴ ይለብስ ዘንድ፥ የአባትህን ቤት ለእኔ መረጥሁት፤ የእስራኤልንም ልጆች የእሳት ቍርባን ሁሉ ስለ ምግብ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።