ለምስጋና የሚሆነውን የደኅንነት መሥዋዕት በአቀረበ ጊዜ እርሾ ያለበትን ኅብስት ያቀርባል።
ለምስጋና ከሚሆነው የኅብረት መሥዋዕት ጋራ፣ በእርሾ የተጋገረ ኅብስት ያቅርብ።
ለምስጋና የሚሆነውን የአንድነት መሥዋዕቱን ባቀረበ ጊዜ እርሾ ያለበትን ኅብስት ያቀርባል።
ከአንድነት መሥዋዕት በተጨማሪ ለመባ የሚሆን በእርሾ ተቦክቶ የተጋገረ ኅብስት ያቅርብ።
ለምስጋና የሚሆነውን የደኅንነት መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ እርሾ ያለበትን ኅብስት ያቀርባል።
የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰማል። የዚያችን ምድር ምርኮኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥” ይላል እግዚአብሔር።
እነዚህንም ዐሥራት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለበጎ መዓዛ በመሠዊያው ላይ አይቀርቡም።
ከየማደሪያችሁ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ከሆነ መልካም የስንዴ ዱቄት የተሠራ ሁለት የቍርባን እንጀራ ታመጣላችሁ፤ ከእህላችሁ ቀዳምያት ለእግዚአብሔር በእርሾ ይጋገራል።
ከኅብስቱም ጋር ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ሰባት ጠቦቶች፥ ከመንጋውም አንድ ወይፈን፥ ሁለትም ነውር የሌለባቸው አውራ በጎች ታቀርባላችሁ፤ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥዋዕት እንዲሆን መሥዋዕታቸውና ቍርባናቸው፥ ወይናቸውም ለእግዚአብሔር ይሁን።
ሕጉን በውጭ አነበባችሁ፤ የታመነም አላችሁት፤ በፈቃዳችሁም የምታቀርቡትን አውጁና አውሩ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም፤