ከእስራኤል ማሰማርያ ከመንጋው ከሁለት መቶው አንዱን የበግ ጠቦት ትሰጣላችሁ፤ ይህ ኀጢአታችሁን ያስተሰርይላችሁ ዘንድ ለእህል ቍርባንና ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለደኅንነትም መሥዋዕት ይሆናል” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ዘሌዋውያን 6:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በመቅደሱ ውስጥ ለማስተስረያ ይሆን ዘንድ ከደሙ ወደ ምስክሩ ድንኳን የሚገባው የኀጢአት መሥዋዕት ሁሉ አይበላም፤ በእሳት ይቃጠላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ደሙ ማስተስረያ እንዲሆን ወደ መገናኛው ድንኳን ወደ ቅድስት የቀረበው የኀጢአት መሥዋዕት ሁሉ በእሳት ይቃጠል እንጂ አይበላ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በመቅደሱ ውስጥ ለማስተስረያ እንዲሆን ከደሙ ወደ መገናኛው ድንኳን የሚገባው የኃጢአት መሥዋዕት ሁሉ አይበላም፤ በእሳት ይቃጠላል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአትን ለማስወገድ በሚደረገው ሥርዓት ደሙ ወደ ድንኳኑ ውስጥ የገባ ከሆነ ግን እንስሳው መበላት የለበትም፤ ሁሉም በእሳት ይቃጠል።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በመቅደሱ ውስጥ ለማስተስረያ ይሆን ዘንድ ከደሙ ወደ መገናኛው ድንኳን የሚገባው የኃጢአት መሥዋዕት ሁሉ አይበላም፤ በእሳት ይቃጠላል። |
ከእስራኤል ማሰማርያ ከመንጋው ከሁለት መቶው አንዱን የበግ ጠቦት ትሰጣላችሁ፤ ይህ ኀጢአታችሁን ያስተሰርይላችሁ ዘንድ ለእህል ቍርባንና ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለደኅንነትም መሥዋዕት ይሆናል” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
እነሆ፥ ደሙን ወደ መቅደስ ውስጥ አላገባችሁትም፤ እኔ እንደታዘዝሁ በቅዱስ ስፍራ ውስጥ ትበሉት ዘንድ ይገባችሁ ነበር።”
በእሳት ከሚቀርበው ከተቀደሰው ይህ ለአንተ ይሆናል፤ ለእኔ የሚያመጡት መባቸው ሁሉ፥ ቍርባናቸውም ሁሉ፥ የኀጢአታቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ የበደላቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ ከተቀደሰውም ሁሉ ለአንተ ለልጆችህም ይሆናል።
ሊቀ ካህናቱ የሚሠዉትን እንስሳ ደም ስለ ኀጢአት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ያቀርብ ነበርና፤ ሥጋውንም ከሰፈር ውጭ ያቃጥሉት ነበር።