በመቅደስም ውስጥ ያገለግል ዘንድ ወደ ውስጠኛው አደባባይ ወደ መቅደሱ በሚገባበት ቀን የኀጢአትን መሥዋዕት ያቅርብ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ዘሌዋውያን 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይም ርኩስነቱን ሳያውቅ ርኩስን ሰው ቢነካ፥ በማናቸውም ርኵሰት ቢረክስ፥ ነገሩ በታወቀ ጊዜ በደል ይሆንበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይም የሰውን ርኩሰት ይኸውም ርኩስ የሚያደርገውን ማንኛውንም ነገር ሳያውቅ ቢነካ፣ ነገሩን ባወቀ ጊዜ በደለኛ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም የረከሰን ሰው በመንካት ከሚያረክስ ከማናቸውም ዓይነት ርኩሰት ሳይታወቀው ነክቶ ቢረክስ፥ ነገሩ በታወቀው ጊዜ በደለኛ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ባለማወቅ ምንም ዐይነት ይሁን ከሰውነት የሚፈስ አንዳች ርኩስ ነገር ቢነካ፥ ያደረገውን ስሕተት ካወቀበት ጊዜ አንሥቶ በደል ይሆንበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም ርኩስነቱን ሳያውቅ ርኩስን ሰው ቢነካ፥ በማናቸውም ርኩሰት ቢረክስ፥ ነገሩ በታወቀው ጊዜ በደል ይሆንበታል። |
በመቅደስም ውስጥ ያገለግል ዘንድ ወደ ውስጠኛው አደባባይ ወደ መቅደሱ በሚገባበት ቀን የኀጢአትን መሥዋዕት ያቅርብ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ካህኑም በሥጋው ቆዳ ያለችውን ያችን ደዌ ይያት፤ ጠጕሯም ተለውጣ ብትነጣ በሥጋው ቆዳ ያለች የዚያች ደዌ መልክ ቢከፋ፥ ደዌውም ወደ ሥጋው ቆዳ ቢጠልቅ፥ እርስዋ የለምጽ ደዌ ናት፤ ካህኑም አይቶ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይበለው።
ርኩስ ነገርን፥ የሞተውን፥ አውሬ የነከሰውን፥ ወይም የበከተ፥ ወይም የሚንቀሳቀስ የእንስሳን በድን የነካ፥ ከእርሱም ያነሣ ሰው ቢኖር፤
ሰው ሳያስብ ክፉን ወይም መልካምን ያደርግ ዘንድ ሳያስብ በከንፈሩ ተናግሮ ቢምል፥ ሳያስብ የማለውም ከዚህ ባንዱ ነገር ቢሆን፥ በታወቀው ጊዜ ከዚህ ነገር በአንዱ በደለኛ ይሆናል።
ከርኩስ ሁሉ፥ ወይም ከረከሰው ሰው፥ ወይም ንጹሕ ካልሆነው እንስሳ የነካች ሰውነት፥ ለእግዚአብሔር ከሆነው ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ብትበላ፥ ያች ሰውነት ከሕዝብዋ ተለይታ ትጥፋ።”