ዘሌዋውያን 4:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በእግዚአብሔር ፊት በመቅደሱ መጋረጃ ፊት ለፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ፣ በመጋረጃው ትይዩ በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ጊዜ ይርጨው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በጌታ ፊት በመጋረጃው ፊት ለፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መቅደሱ መጋረጃ ፊት ለፊት ሆኖ ደሙን በጣቱ እያጠቀሰ ሰባት ጊዜ በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ይርጨው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በእግዚአብሔር ፊት በመጋረጃው ፊት ለፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። |
ከወይፈኑም ደም ወስዶ በስርየቱ መክደኛ ላይ ወደ ምሥራቅ በጣቱ ይረጨዋል፤ ከደሙም በመክደኛው ፊት በጣቱ ሰባት ጊዜ ይረጫል።
ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀባ፤ ድንኳኒቱንና ዕቃዋን ሁሉ ቀብቶ ቀደሳቸው።