ዘሌዋውያን 27:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእግዚአብሔርም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው እንስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእነዚህ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ሰውየው የተሳለው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሆኖ መቅረብ የሚችል እንስሳ ከሆነ፣ እንዲህ ያለው ለእግዚአብሔር የተሰጠ እንስሳ የተቀደሰ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለጌታም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው እንስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእነዚህ ለጌታ የሚሰጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስእለቱ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበው እንስሳ ከሆነ አይዋጅም፤ ለእግዚአብሔር የቀረበው መባ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔርም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው እንስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእነዚህ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል። |
ለሥጋህ በደል አፍህን አትስጥ፥ በእግዚአብሔርም ፊት፥ “ባለማወቅ ነው” አትበል፤ እግዚአብሔር ስለ ቃልህ እንዳይቈጣ፥ የእጅህንም ሥራ እንዳያጠፋብህ፤
ለግምቱ የሚከፍለውን ቢያጣ ግን በካህኑ ፊት ይቁም፤ ካህኑም የተሳለውን ሰው ከእጁ ባለው ገንዘብ መጠን ይገምትለት፤ ካህኑም የተሳለው ሰው እንደሚችል መጠን ይገምትለት።
“ሰው ቢዘነጋ፥ ሳያውቅም ለእግዚአብሔር በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኀጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ከመንጋዉ ነውር የሌለበትን እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተገመተውን አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት ያቀርባል።