በጨለማም ወደ ሶርያውያን ሰፈር ይሄዱ ዘንድ ተነሡ፤ ወደ ሶርያውያንም ሰፈር መጀመሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በዚያ ማንም ሰው አልነበረም።
ዘሌዋውያን 27:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለግምቱ የሚከፍለውን ቢያጣ ግን በካህኑ ፊት ይቁም፤ ካህኑም የተሳለውን ሰው ከእጁ ባለው ገንዘብ መጠን ይገምትለት፤ ካህኑም የተሳለው ሰው እንደሚችል መጠን ይገምትለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስእለት የተሳለው ድኻ ከሆነና ግምቱን መክፈል ካልቻለ ግን፣ ለስጦታ ያሰበውን ሰው ወደ ካህኑ ያምጣ፤ ካህኑም የተሳለው ሰው ባለው ዐቅም መሠረት መክፈል የሚገባውን ይተምንለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማናቸውም ሰው ለግምትህ ከድህነቱ የተነሣ የሚከፍለውን ቢያጣ እርሱም በካህኑ ፊት የስለቱን ሰው የምጣው፥ ካህኑም እርሱን ይገምተው፤ ካህኑም የተሳለው ሰው አቅሙ እንደሚፈቅደው መጠን ይገምትለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስእለት ያደረገው ሰው ይህን ተመን ለመክፈል የማይችል ሆኖ ከተገኘ ያ ለስጦታ የቀረበውን ሰው ወደ ካህኑ ያምጣው፤ ካህኑም ያ ሰው የሚችለውን ያኽል ገምቶ ዝቅተኛ ዋጋ ያስከፍለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለግምቱም የሚከፍለውን ቢያጣ ግን በካህኑ ፊት ይቁም፥ ካህኑም የተሳለውን ሰው ይገምተው፤ ካህኑም የተሳለው ሰው እንደሚችል መጠን ይገምተው። |
በጨለማም ወደ ሶርያውያን ሰፈር ይሄዱ ዘንድ ተነሡ፤ ወደ ሶርያውያንም ሰፈር መጀመሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በዚያ ማንም ሰው አልነበረም።
“ከእነዚህ ነገሮች በየትኛው ይቅር እልሻለሁ? ልጆችሽ ትተውኛል፤ አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል፤ አጠገብኋቸውም፤ እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ በአመንዝራዎቹም ቤት ዐደሩ።
ጠቦት ለማምጣት የሚበቃ ገንዘብ በእጅዋ ባይኖራት ሁለት ዋኖሶች፥ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለኀጢአት መሥዋዕት ታቀርባለች፤ ካህኑም ያስተሰርይላታል፤ እርስዋም ትነጻለች።”
“ለእግዚአብሔርም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው እንስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእነዚህ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።
“ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ለማምጣት ገንዘብ በእጁ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኀጢአት የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ ክፍል መልካም የስንዴ ዱቄት ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርባል፤ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና ዘይት አያፈስስበትም፤ ዕጣንም አይጨምርበትም።
“ስለ ሠራው ኀጢአት የበግ መግዣ ገንዘብ በእጁ ባይኖረው ግን፥ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእግዚአብሔር ያቀርባል። ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤
ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም።