የአሞንም ልጆች ሶርያውያን ከኢዮአብ ፊት እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ከወንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሹ፤ ወደ ከተማዪቱም ገቡ። ኢዮአብም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
ዘሌዋውያን 26:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፤ በፊታችሁም በሰይፍ ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ እነርሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በእናንተም ፊት በሰይፍ ይወድቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ በፊታችሁም በጦርነት ያልቃሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በፊታችሁም በሰይፍ ይወድቃሉ። |
የአሞንም ልጆች ሶርያውያን ከኢዮአብ ፊት እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ከወንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሹ፤ ወደ ከተማዪቱም ገቡ። ኢዮአብም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ ፤
በምድራችሁም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፤ ትተኛላችሁ፤ የሚያስፈራችሁም የለም፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድራችሁ አጠፋለሁ።
ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፤ መቶውም ዐሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
“እግዚአብሔርም ከእግርህ በታች ይወድቁ ዘንድ የሚቃወሙህን ጠላቶችህን በእጅህ ይጥላቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፤ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ።
አንዱ ሽሁን እንዴት ያሳድዳቸዋል? ሁለቱስ ዐሥሩን ሽህ እንዴት ያባርሩአቸዋል? እግዚአብሔር ፍዳውን አምጥቶባቸዋልና። አምላካችንም አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና።
ባርቅም ሰረገሎችንና ሠራዊቱን እስከ አሕዛብ አሪሶት ድረስ አባረረ፤ የሲሣራም ሠራዊት ሁሉ በሰይፍ ስለት ወደቀ፤ አንድ እንኳ አልቀረም።
ዮናታንም በእጁና በእግሩ ወጣ፤ ጋሻ ጃግሬውም ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ዮናታንም ፊቱን መልሶ ገደላቸው፤ ጋሻ ጃግሬውም ተከትሎ ገደላቸው።