Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 14:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዮና​ታ​ንም በእ​ጁና በእ​ግሩ ወጣ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ዮና​ታ​ንም ፊቱን መልሶ ገደ​ላ​ቸው፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም ተከ​ትሎ ገደ​ላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዮናታን በእጁና በእግሩ ተፍጨርጭሮ፣ ጋሻ ጃግሬውን በማስከተል ወጣ። ፍልስጥኤማውያንም በዮናታን እጅ ወደቁ፤ ጋሻ ጃግሬውም ከበስተኋላው እየተከተለ ገደላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዮናታን በእጁና በእግሩ ወደ አፋፉ፥ ጋሻ ጃግሬውን በማስከተል ወጣ። በዮናታንም እጅ ወደቁ፤ ጋሻ ጃግሬውም ከበስተኋላው እየተከተለ ገደላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዮናታንም በእጁና በጒልበቱ እየዳኸ ወደ አፋፉ ወጣ፤ ጋሻጃግሬውም ተከተለው፤ ዮናታንም በፍልስጥኤማውያን ላይ ድንገተኛ አደጋ በመጣል መታቸው፤ ጋሻጃግሬውም ገደላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዮናታንም በእጁና በእግሩ ወጣ፥ ጋሻ ጃግሬውም ተከተለው፥ ፍልስጥኤማውያንም በዮናታን እጅ ወደቁ፥ ጋሻ ጃግሬውም ተከትሎ ገደላቸው።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 14:13
10 Referencias Cruzadas  

የእ​ሳት ኀይ​ልን አጠፉ፤ ከሰ​ይፍ ስለት አመ​ለጡ፤ ከድ​ካ​ማ​ቸው በረቱ፤ በጦ​ር​ነት ኀይ​ለ​ኞች ሆኑ፤ የባ​ዕድ ጭፍ​ሮ​ች​ንም አባ​ረሩ።


እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረን ስለ እና​ንተ የሚ​ዋጋ እርሱ ነውና ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳ​ድ​ዳል።


አንዱ ሽሁን እን​ዴት ያሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል? ሁለ​ቱስ ዐሥ​ሩን ሽህ እን​ዴት ያባ​ር​ሩ​አ​ቸ​ዋል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍዳ​ውን አም​ጥ​ቶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና። አም​ላ​ካ​ች​ንም አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ግ​ርህ በታች ይወ​ድቁ ዘንድ የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ህን ጠላ​ቶ​ች​ህን በእ​ጅህ ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ይመ​ጡ​ብ​ሃል፤ በሰ​ባ​ትም መን​ገድ ከፊ​ትህ ይሸ​ሻሉ።


እር​ሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግ​ሬ​ውን ጠርቶ፥ “ሴት ገደ​ለ​ችው እን​ዳ​ይሉ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ግደ​ለኝ” አለው፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ወጋው፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ሞተ።


የሰ​ፈ​ሩም ሰዎች፦ ዮና​ታ​ን​ንና ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን “ወደ እኛ ውጡ፤ አንድ ነገ​ር​ንም እን​ነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለን” አሉ። ዮና​ታ​ንም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ተከ​ተ​ለኝ” አለው።


የዮ​ና​ታ​ንና የጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በወ​ን​ጭ​ፍና በዱላ የመ​ጀ​መ​ሪያ ግድ​ያ​ቸው በአ​ንድ ትልም እርሻ መካ​ከል ሃያ ያህል ሰው ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios