ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፤ ከሰውም እጅ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።
ዘሌዋውያን 24:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውንም የመታና የገደለ ፈጽሞ ይገደል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንስሳ የገደለ ማንኛውም ሰው በገደለው ፈንታ ይተካ፤ ሰው የገደለ ግን ይገደል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንስሳንም የሚገድል በካሣ ይተካ፤ ሰውን ግን የሚገድል ይገደል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንስሳ የሚገድል ምትኩን ይክፈል፤ ሰውን የሚገድል ግን በሞት ይቀጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንስሳውንም የሚገድል ካሣ ይተካ፤ ሰውንም የሚገድል ይገደል። |
ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፤ ከሰውም እጅ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።
እርሱ ቢበድልና ከዚህ በኋላ ንስሓ ቢገባ፥ በቅድሚያ የወሰደውን፥ ወይም በዐመፅና በግፍ የተቀበለውን፥ ወይም የተሰጠውን አደራ፥ ወይም ጠፍቶ ያገኘውን፥