ዘሌዋውያን 23:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ መጨረሻዋ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ አምሳ ቀን ቍጠሩ፤ አዲሱንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ ሰባተኛው ሰንበት ማግስት ድረስ ዐምሳ ቀን ቍጠሩ፤ ከዚያም የአዲስ እህል ቍርባን ለእግዚአብሔር አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ ኀምሳ ቀን ቁጠሩ። ከዚያም አዲሱን የእህል ቁርባን ለጌታ አቅርቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰባተኛው ሰንበት በኋላ በኀምሳኛው ቀን እንደገና የአዲስ እህል ቊርባን ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ አምሳ ቀን ቍጠሩ፤ አዲሱንም የእህል ቍርባን ወደ እግዚአብሔር አቅርቡ። |
ከየማደሪያችሁ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ከሆነ መልካም የስንዴ ዱቄት የተሠራ ሁለት የቍርባን እንጀራ ታመጣላችሁ፤ ከእህላችሁ ቀዳምያት ለእግዚአብሔር በእርሾ ይጋገራል።
“በበዓለ ሠዊት ቀን በሰንበታት በዓላችሁ አዲሱን የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ባቀረባችሁ ጊዜ፥ የተቀደሰ ቀን ይሆንላችኋል፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።