በአሮንም ግንባር ላይ ይሆናል፤ አሮንም የእስራኤል ልጆች በሚያቀርቡትና በሚቀድሱት በቅዱሱ ስጦታቸው ሁሉ ላይ የሠሩትን ኀጢአት ይሸከም፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀባይነት ያለው እንዲሆንላቸው ሁልጊዜ በግንባሩ ላይ ይሁን።
ዘሌዋውያን 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ነዶውን በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምርላችሁ ያቀርበዋል፤ በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ካህኑ ያቅርበው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነዶው ተቀባይነት እንዲያገኝላችሁም በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዘው፤ ካህኑ ነዶውን የሚወዘውዘው በሰንበት ቀን ማግስት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ነዶውን በጌታ ፊት እንዲሠምርላችሁ ይወዝውዘው፤ ካህኑ የሚወዘውዘው በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ይቀበላችሁ ዘንድ ካህኑ ነዶውን በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቀርባል። ካህኑም እርሱን ማቅረብ ያለበት ከሰንበት ቀጥሎ በሚውለው ቀን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ነዶውን በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምርላችሁ ይወዝውዘው፤ በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ካህኑ ይወዝውዘው። |
በአሮንም ግንባር ላይ ይሆናል፤ አሮንም የእስራኤል ልጆች በሚያቀርቡትና በሚቀድሱት በቅዱሱ ስጦታቸው ሁሉ ላይ የሠሩትን ኀጢአት ይሸከም፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀባይነት ያለው እንዲሆንላቸው ሁልጊዜ በግንባሩ ላይ ይሁን።
እነዚህም ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕቶች ለአንተና ለልጆችህ ሥርዐት እንዲሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የመሥዋዕቱን ፍርምባና ወርች አንተ፥ ከአንተ ጋርም ልጆችህ፥ ቤተሰብህም ተለይቶ በንጹሕ ስፍራ ትበላላችሁ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ መከሩንም ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤
ነዶውንም ባቀረባችሁበት ቀን ነውር የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ።