ዘሌዋውያን 22:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ከተቀደሰው ቢበላ አምስተኛ እጅ ጨምሮ የተቀደሰውን ለካህኑ ይስጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ማንኛውም ሰው ባለማወቅ የተቀደሰውን መሥዋዕት ቢበላ፣ የመሥዋዕቱን አንድ ዐምስተኛ ጨምሮ ለካህኑ ይተካ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ከተቀደሰው ነገር ቢበላ በፊት በነበረው ላይ አምስት እጅ ጨምሮ የተቀደሰውን ነገር ለካህኑ ይስጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የካህን ቤተሰብ ያልሆነ ማንም ሰው ባለማወቅ ከተቀደሰው ስጦታ በልቶ ቢገኝ የምግቡን ሙሉ ዋጋና አንድ አምስተኛ እጅ ጨምሮ ለካህኑ ይክፈለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ከተቀደሰው ቢበላ አምስተኛ እጅ ጨምሮ የተቀደሰውን ለካህኑ ይስጥ። |
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሳያውቅ በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥