የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ መንግሥትን ለዳዊትና ለልጆቹ በጨው ቃል ኪዳን ለዘለዓለም እንደ ሰጠ በውኑ አታውቁምን?
ዘሌዋውያን 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምታቀርቡት ቍርባን ሁሉ በጨው ይጣፈጣል፤ የአምላክህም ቃል ኪዳን ጨው ከቍርባንህ አይጕደል፤ በቍርባናችሁ ሁሉ ላይ ጨው ትጨምራላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምታቀርበውን የእህል ቍርባን ሁሉ በጨው ቀምመው፤ የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቍርባንህ አይታጣ፤ በቍርባንህም ላይ ጨው ጨምርበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምታቀርበውን የእህል ቁርባን ሁሉ በጨው ታጣፍጠዋለህ፤ የአምላክህንም የቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቁርባንህ እንዳታጐድል፤ በቁርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ታቀርባለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ የእህል ቊርባን ስለ ሆነ በእህል ቊርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ጨምርበት፤ የአምላክህን የጨው ቃል ኪዳን አትተው፤ በቊርባኖች ሁሉ ጨው መግባት አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምታቀርበውን የእህል ቍርባን ሁሉ በጨው ታጣፍጠዋለህ፤ የአምላክህንም ቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቍርባንህ አታጐድልም፤ በቍርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ታቀርባለህ። |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ መንግሥትን ለዳዊትና ለልጆቹ በጨው ቃል ኪዳን ለዘለዓለም እንደ ሰጠ በውኑ አታውቁምን?
እስከ መቶ መክሊት ብርም ቢሆን፥ እስከ መቶም የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ ዘይት ቢሆን፥ ጨውም ያለ ልክ ቢሆን፤
በእግዚአብሔርም ፊት ታቀርባቸዋለህ፤ ካህናቱም ጨው ይጨምሩባቸዋል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር ያቀርቡአቸዋል።
የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር የሚለዩትን የተቀደሰውን መባ ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ሰጥቼሃለሁ፤ ይህም ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በእግዚአብሔር ፊት የዘለዓለም ሕግና የሁልጊዜ ቃል ኪዳን ነው።”