ዘሌዋውያን 19:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበላውም ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና ኀጢአቱን ይሸከማል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመሥዋዕቱ የሚበላ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ነገር አርክሷልና ይጠየቅበታል፤ ያም ሰው ከወገኑ ተለይቶ ይጥፋ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱንም የሚበላ ማናቸውም ሰው ለጌታ የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና በደሉን ይሸከማል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱ የሚበላ ማንም ሰው ለእኔ የተቀደሰውን እንደ ተራ ነገር በመቊጠሩ በደል ይሆንበታል፤ ከሕዝቤም ይለያል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበላውም ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና ኃጢአቱን ይሸከማል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ። |
“የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን አጨዳ አታጥሩ፤ ስታጭዱም የወደቀውን ቃርሚያ አትልቀሙ።
“አንድ ሰው ቢበድል፥ የሚያምለውንም ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይናገር በደሉን ይሸከማል፤
ኀጢአት ሳለባት፥ ለእግዚአብሔር ከሆነው ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ የበላች ሰውነት፥ ያች ሰውነት ከሕዝብዋ ተለይታ ትጥፋ።
ከርኩስ ሁሉ፥ ወይም ከረከሰው ሰው፥ ወይም ንጹሕ ካልሆነው እንስሳ የነካች ሰውነት፥ ለእግዚአብሔር ከሆነው ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ብትበላ፥ ያች ሰውነት ከሕዝብዋ ተለይታ ትጥፋ።”