መልካሙን የስንዴ ዱቄት ብታመጡ እንኳ ከንቱ ነው፤ ዕጣናችሁ በእኔ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ መባቻዎቻችሁንና ሰንበቶቻችሁን፥ ታላቋን፥ ቀናችሁን፥ ጾማችሁንና ሥራ መፍታታችሁን አልወድም።
ዘሌዋውያን 19:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሦስተኛውም ቀን ቢበላ ጸያፍ ነው፤ ተቀባይነት የለውም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛውም ቀን ቢበላ ርኩስ ነው፤ ተቀባይነትም የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሦስተኛውም ቀን ቢበላ ጸያፍ ነው፥ እርሱም ተቀበባይነት አይኖረውም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሦስተኛው ቀን ቢበላ ርኩስ ነው፤ መሥዋዕቱም ተቀባይነት አይኖረውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሦስተኛውም ቀን ቢበላ ጸያፍ ነው፥ ደስም አያሰኝም፤ |
መልካሙን የስንዴ ዱቄት ብታመጡ እንኳ ከንቱ ነው፤ ዕጣናችሁ በእኔ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ መባቻዎቻችሁንና ሰንበቶቻችሁን፥ ታላቋን፥ ቀናችሁን፥ ጾማችሁንና ሥራ መፍታታችሁን አልወድም።
በመቃብርም መካከል የሚተኙ፥ በዋሻ ውስጥ የሚያልሙ፥ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። የመሥዋዕታቸውን ደምና ዕቃቸውንም ሁሉ ያረክሳሉ።
በሬን የሚሠዋልኝ ኃጥእ ውሻን እንደሚያርድልኝ ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብም የእሪያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንንም ለመታሰቢያ የሚያጥን አምላክን እንደሚፀርፍ ነው፤ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል።
ምድሬንም በተጠሉ በጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኀጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”
የበላውም ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና ኀጢአቱን ይሸከማል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።
በሬው፥ ወይም በጉ ጆሮው፥ ወይም ጅራቱ የተቈረጠ ቢሆን፥ ቈጥረህ የራስህ ገንዘብ አድርገው እንጂ ለስእለት አይቀበልህም።
ከእነዚህም ከባዕድ ወገን ከሆነ ሰው እጅ ለአምላካችሁ መባ አታቅርቡ፤ ርኵሰትም፥ ነውርም አለባቸውና አይቀበላችሁም።”