ዘሌዋውያን 18:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኅቷ ላይ እንዳትቀና ሚስትህ በሕይወት ሳለች የእኅቷን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ሚስትህ በሕይወት እያለች እኅቷን ጣውንት አድርገህ አታግባት፤ ከርሷም ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኅትዋ በሕይወት እስካለች ድረስ ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ የእርሷን እኅት እንደ ሁለተኛ ሚስት አድርገህ አታግባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስትህ በሕይወት እያለች እኅትዋ ጣውንትዋ እንዳትሆን እኅትዋን አታግባ፤ ከእርስዋም ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚስትህ በሕይወት ሳለች እኅትዋ ጣውንትዋ እንዳትሆን፥ ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ከእርስዋ ጋር እኅትዋን አታግባ። |
ልያም፥ “ባሌን መውሰድሽ አይበቃሽምን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይደር” አለች፤ ሰጠቻትም።
አምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ፤ ሌሎችም አምስት መጋረጃዎች እንዲሁ እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ።።
የሴትንና የሴት ልጅዋን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጅዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅዋን ሴት ልጅ ኀፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ኀጢአት ነውና።
እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድር ነው? ዘር አይደለምን? ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።