በዚያም ዳዊት ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትንም አቀረበ። ሰሎሞንም በኋላ ዘመን በመሠዊያው ላይ ጨመረ፤ ያንጊዜ አነስተኛ ነበርና። እግዚአብሔርም ስለ ሀገሪቱ የተለመነውን ሰማ፤ መቅሠፍቱም ከእስራኤል ተከለከለ።
ዘሌዋውያን 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእነርሱ እንዲህ በላቸው፥ “ከእስራኤል ቤት ከመካከላቸው ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲህም በላቸው፤ ‘የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእነርሱም እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ቤት በመካከላቸውም ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእነርሱም እንዲህ በላቸው፦ ‘ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በማኅበሩ መካከል የሚኖር መጻተኛ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእነርሱም እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ቤት በመካከላቸውም ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥ |
በዚያም ዳዊት ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትንም አቀረበ። ሰሎሞንም በኋላ ዘመን በመሠዊያው ላይ ጨመረ፤ ያንጊዜ አነስተኛ ነበርና። እግዚአብሔርም ስለ ሀገሪቱ የተለመነውን ሰማ፤ መቅሠፍቱም ከእስራኤል ተከለከለ።
“ከእስራኤልም ልጆች፥ ወይም በመካከላቸው ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ያንም ሰው ከሕዝቡ ለይች አጠፋዋለሁ።
ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የተመረጠ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ወይም የድኅነት መሥዋዕት ያደርገው ዘንድ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ በሌላም ቦታ ቢያርደው፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ለእግዚአብሔር ቍርባን ያቀርብ ዘንድ ወደ ምስክሩ ድንኳን ባያመጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈጠርበታል፤ ደም አፍስሶአልና፤ ያም ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።
መሥዋዕታቸውንም ደግሞ ተከትለው ላመነዘሩባቸው ለሰይጣናት አይሠዉ። ይህ ለእነርሱ ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።”
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በገለዓድ፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ እንደ ሠሩ ሰሙ።
በገለዓድም ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ ደረሱ፤ እንዲህም ብለው ነገሩአቸው
የእግዚአብሔር ማኅበር ሁሉ የሚለው ይህ ነው፥ “ዛሬ እግዚአብሔርን መከተልን ትተዉ ዘንድ፥ መሠዊያም ትሠሩ ዘንድ፥ እግዚአብሔርንም ዛሬ ትክዱት ዘንድ ይህ በእስራኤል አምላክ ፊት ያደረጋችሁት ኀጢአት ምንድን ነው?
በዚያም ተራራ አናት ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ አሳምረህ ሥራ፤ ሁለተኛዉንም በሬ ውሰድ፤ በዚያም በቈረጥኸው በማምለኪያ ዐጸዱ እንጨት ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርብ” አለው።
በፊቴም ወደ ጌልገላ ትወርዳለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወርዳለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስክመጣና የምታደርገውን እስከምነግርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈያለህ።”
ሳሙኤልም፥ “እንዴት እሄዳለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ‘ለእግዚአብሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ’ በል።
ሳሙኤልም አንድ የበግ ጠቦት ወስዶ ለእግዚአብሔር ፈጽሞ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ከሕዝቡ ጋር አቀረበው፤ ሳሙኤልም ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው።