ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፤ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።
ዘሌዋውያን 15:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህንም ነገሮች የሚነካ ሁሉ ርኩስ ነው፤ ልብሱንም ያጥባል፤ በውኃም ይታጠባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህንም የሚነካ ማንኛውም ሰው ርኩስ ይሆናል፤ ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህንም ነገሮች የሚነካ ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ ልብሱንም ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱንም የሚነካ ሁሉ ስለሚረክስ ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱን ታጥቦ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህንም ነገሮች የሚነካ ሁሉ ርኩስ ነው፤ ልብሱንም ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው። |
ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፤ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።
“ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው ከፈሳሹ ነገር ሲነጻ ስለ መንጻቱ ሰባት ቀን ይቈጥራል፤ ልብሶቹንም ያጥባል፤ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠባል፤ ንጹሕም ይሆናል።
ደምዋም በሚፈስስበት ወራት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በግዳጅዋ ጊዜ እንደ ነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ እንደ ግዳጅዋ ርኩስነት ርኩስ ነው።
እንግዲህ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ።
ነውር የሌለው ሆኖ፥ በዘለዓለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናመልከው ዘንድ ሕሊናችንን ከሞት ሥራ እንዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።