ዘሌዋውያን 15:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘር የነካው ልብስ ሁሉ፥ ቍርበትም ሁሉ በውኃ ይታጠባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈሰሰው ዘር የነካው ማንኛውም ልብስ ወይም ቍርበት በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘሩ የነካው ልብስ ሁሉ ቆዳም ሁሉ በውኃ ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘሩ የፈሰሰበት ማንኛውም ልብስም ሆነ ቆዳ በውሃ ይታጠብ እርሱም እስከ ምሽት ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘር የነካው ልብስ ሁሉ ቍርበትም ሁሉ በውኃ ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው። |
ከአሮን ዘር ለምጽ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት ሁሉ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ከተቀደሰው አይብላ። ከበድንም የተነሣ ርኩስ የሆነውን፥ ወይም ዘሩ ከእርሱ የሚፈስስበትን የሚነካ፥
በእሳት ለማለፍ የሚችለው ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ ይሆናል፤ ነገር ግን በማንጻት ውኃ ደግሞ ይጠራል። በእሳትም ለማለፍ የማይችለውን በውኃ ታሳልፉታላችሁ።