እኔስ በጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ነኝ የእግዚአብሔር ይቅርታው በጊዜው ነው፤ ይቅርታህ ብዙ ሲሆን መድኃኒቴ ሆይ፥ በእውነት አድነኝ።
ዘሌዋውያን 14:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ዋኖሶች፥ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች በእጁ እንዳገኘ አንዲቱን ለኀጢአት መሥዋዕት፥ አንዲቱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ይወስዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ዐቅሙ የፈቀደውን አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመግዛትም አቅሙ የሚፈቅድለትን ያህል ሁለት ዋኖሶች ወይም የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያደርገዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ችሎታው በሚፈቅድለት መጠን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንዱን ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያመጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት ዋኖሶች ወይም የርግብ ግልገሎች እንደሚቻለው፥ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ይወስዳል። |
እኔስ በጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ነኝ የእግዚአብሔር ይቅርታው በጊዜው ነው፤ ይቅርታህ ብዙ ሲሆን መድኃኒቴ ሆይ፥ በእውነት አድነኝ።
ከእነርሱም የሚሸሹ ይድናሉ፤ መብረርን እንደሚማር ርግብም በተራራ ላይ ይሆናሉ፤ እኔም በኀጢአታቸው ሁሉ እገድላለሁ።
“ድሃም ቢሆን፥ በእጁም ገንዘብ ባይኖረው፥ ማስተስረያ ይሆንለት ዘንድ አንድ ጠቦት ስለ በደል የመለየት መሥዋዕት፥ ከመስፈሪያውም ከዐሥር እጅ አንድ እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ የስንዴ ዱቄት ለቍርባን፥ አንድ ማሰሮ ዘይትም ያመጣል።
ካህኑም የበደሉን መሥዋዕት የበግ ጠቦት የማሰሮውንም ዘይት ይወስዳል፤ በእግዚአብሔርም ፊት ለቍርባን ያቀርበዋል።
በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ይዞ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያመጣል፤ ለካህኑም ይሰጠዋል።
“ስለ ሠራው ኀጢአት የበግ መግዣ ገንዘብ በእጁ ባይኖረው ግን፥ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእግዚአብሔር ያቀርባል። ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤