ዘሌዋውያን 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ በሰባተኛው ቀን ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ያች ደዌ ብትከስም፥ በቆዳውም ላይ ባትሰፋ፥ ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለዋል፤ ምልክት ነውና፥ ልብሱንም አጥቦ ንጹሕ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰባተኛው ቀን ካህኑ እንደ ገና ይመርምረው፤ ቍስሉ ከከሰመና በቈዳው ላይ ካልተስፋፋ፣ ካህኑ ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ፤ ቍስሉ ችፍታ እንጂ ሌላ አይደለም። ሰውየው ልብሱን ይጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባተኛውም ቀን ካህኑ ዳግም ያየዋል፤ እነሆም፥ ደዌው ቢከስም፥ ደዌውም በቆዳው ላይ ባይሰፋ፥ ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፤ እከክ ነው፤ ልብሱንም ያጥብና ንጹሕ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም እንደገና በሰባተኛው ቀን ይመርምረው፤ በሚመረምረውም ጊዜ ቊስሉ በመስፋፋት ፈንታ ከስሞ ከተገኘ፥ ቊስሉ እከክ ብቻ መሆኑን ገልጦ ያ ሰው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ፤ ያም ሰው ስለ መንጻቱ ልብሱን ይጠብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ በሰባተኛው ቀን ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ደዌው ቢከስም፥ ደዌውም በቁርበቱ ላይ ባይሰፋ፥ ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፤ እከክ ነው፤ ልብሱንም አጥቦ ንጹሕ ይሆናል። |
ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ በድኑንም የሚያነሣ፤ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።
“ሰው በሥጋው ቆዳ ላይ እባጭ ብትወጣበት፥ ብትነጣም፥ በሥጋውም ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ብትመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካህናቱ ልጆች ወደ አንዱ ያምጡት።
በሰባተኛውም ቀን ካህኑ ያችን ደዌ ይያት፤ እነሆም፥ ያች ደዌ በፊት እንደ ነበረች ብትሆን፥ በቆዳውም ላይ ባትሰፋ፥ ካህኑ ሰባት ቀን ደግሞ ይለየዋል።
የነጻውም ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ጠጕሩንም ሁሉ ይላጫል፤ በውኃም ይታጠባል፤ ንጹሕም ይሆናል። ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀመጣል።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለሆን ራሳችንን እናንጻ፤ ሥጋችንን አናርክስ፤ ነፍሳችንንም አናሳድፍ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት የምንቀደስበትን እንሥራ።
እንግዲህ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ።
እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥምቀትም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዐቶች ብቻ ናቸው።