በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ይለዩ ዘንድ ሕዝቤን ያስተምሩ፤ ንጹሕና ንጹሕ ባልሆነው መካከል ይለዩ ዘንድ ያሳዩአቸው።
ዘሌዋውያን 13:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ደዌውን አይቶ ደዌው ያለበትን ነገር ሰባት ቀን ይለየዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ደዌውን ይመርምር፤ በደዌ የተበከለውንም ዕቃ ሰባት ቀን ያግልል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ደዌውን ያያል፤ ደዌውም ያለበትን ነገር ሰባት ቀን ለይቶ ያስቀምጠዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም ይመርምረውና እነዚህ ሁሉ የልብስ ዐይነቶች እስከ ሰባት ቀን ድረስ በአንድ ክፍል ተዘግቶባቸው ይቈዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ደዌውን አይቶ ደዌው ያለበትን ነገር ሰባት ቀን ይዘጋበታል። |
በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ይለዩ ዘንድ ሕዝቤን ያስተምሩ፤ ንጹሕና ንጹሕ ባልሆነው መካከል ይለዩ ዘንድ ያሳዩአቸው።
ቋቍቻውም በሥጋው ቆዳ ላይ ቢነጣ፥ ከቆዳውም የጠለቀ ባይመስል፥ ጠጕሩም ባይነጣ፥ ካህኑ የታመመውን ሰው ሰባት ቀን ይዘጋበታል።
ደዌው በልብሱ ወይም በቆዳው ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በሚደረገው ነገር አረንጓዴ ወይም ቀይ ቢሆን፥ የለምጽ ደዌ ነው፤ ለካህኑ ያሳያል።
በሰባተኛውም ቀን ደዌውን ያያል፤ ደዌውም በልብስ ላይ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም በቆዳው ወይም ከቆዳው በሚደረግ ነገር ቢሰፋ፥ ደዌው እየፋገ የሚሄድ ለምጽ ነው፤ ርኩስ ነው።