እርሱም አለው፥ “የሦስት ዓመት ላም፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም አምጣ፤ እኒህንም ሁሉ አምጥተህ ከሁለት ከሁለት ቍረጣቸው፤ ወፎችን ግን አትቍረጣቸው።”
ዘሌዋውያን 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእግዚአብሔርም የሚያቀርበው ቍርባን የሚቃጠል መሥዋዕት ከዎፎች ቢሆን፥ ቍርባኑን ከዋኖስ ወይም ከርግብ ያቀርባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ለእግዚአብሔር በሚቃጠል መሥዋዕትነት የሚቀርበው መባ ከወፎች ወገን ከሆነ፣ ዋኖስ ወይም የርግብ ጫጩት ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለጌታም የሚቀርበው ቁርባን የሚቃጠል መሥዋዕት ከወፎች ቢሆን፥ ቁርባኑን ከዋኖስ ወይም ከርግብ ያቀርባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየው፥ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ማቅረብ የፈለገው መባ ከወፎች ወገን ከሆነም የርግብ ጫጩት ወይም ዋኖስ መሆን ይችላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔርም የሚቀርበው ቍርባን የሚቃጠል መሥዋዕት ከወፎች ቢሆን፥ ቍርባኑን ከዋኖስ ወይም ከርግብ ያቀርባል። |
እርሱም አለው፥ “የሦስት ዓመት ላም፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም አምጣ፤ እኒህንም ሁሉ አምጥተህ ከሁለት ከሁለት ቍረጣቸው፤ ወፎችን ግን አትቍረጣቸው።”
ጠቦት ለማምጣት የሚበቃ ገንዘብ በእጅዋ ባይኖራት ሁለት ዋኖሶች፥ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለኀጢአት መሥዋዕት ታቀርባለች፤ ካህኑም ያስተሰርይላታል፤ እርስዋም ትነጻለች።”
እንደ ሥርዐቱም ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያዘጋጀዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይሰረይለታል።
“ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ለማምጣት ገንዘብ በእጁ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኀጢአት የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ ክፍል መልካም የስንዴ ዱቄት ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርባል፤ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና ዘይት አያፈስስበትም፤ ዕጣንም አይጨምርበትም።
“ስለ ሠራው ኀጢአት የበግ መግዣ ገንዘብ በእጁ ባይኖረው ግን፥ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእግዚአብሔር ያቀርባል። ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤
ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና
በእግዚአብሔርም ሕግ እንደ ታዘዘ ሁለት ዋኖስ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ስለ እርሱ መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡለት ዘንድ።
ቅዱስና ያለ ተንኰል፥ ነውርም የሌለበት፥ ከኀጢአተኞችም የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል።