“አቤቱ፥ ይህን አደርግ ዘንድ ከእኔ ይራቅ፤ ነፍሳቸውን ሰጥተው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?” ብሎ ይጠጣ ዘንድ አልወደደም። ሦስቱ ኀያላንም ያደረጉት ይህ ነው።
ሰቈቃወ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምድረ በዳ ሰይፍ የተነሣ፥ በሕይወታችን እንጀራችንን እናመጣለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድረ በዳ ካለው ሰይፍ የተነሣ፣ በሕይወታችን ተወራርደን እንጀራ አገኘን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምድረበዳ ሰይፍ የተነሣ በሕይወታችን እንጀራችንን እናመጣለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በበረሓው ግድያ ስላለ ምግባችንን ማግኘት የምንችለው ሕይወታችንን ለአደጋ በማጋለጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምድረ በዳ ሰይፍ የተነሣ በሕይወታችን እንጀራችንን እናመጣለን። |
“አቤቱ፥ ይህን አደርግ ዘንድ ከእኔ ይራቅ፤ ነፍሳቸውን ሰጥተው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?” ብሎ ይጠጣ ዘንድ አልወደደም። ሦስቱ ኀያላንም ያደረጉት ይህ ነው።
እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በሀገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለ ገደለው ከለዳውያንን ፈርተዋልና።
እናንተም፦ አይደለም፤ ሰልፍ ወደማናይባት፥ የመለከትም ድምፅ ወደማንሰማባት፥ እንጀራንም ወደማንራብባት ወደ ግብፅ ምድር እንሄዳለን፤ በዚያም እንቀመጣለን ብትሉ፥
እናንተ የምትፈሩት ሰይፍ በዚያ በግብፅ ምድር ያገኛችኋል፤ ስለ እርሱም የምትደነግጡበት ራብ በዚያ በግብፅ ይደርስባችኋል፤ በዚያም ትሞታላችሁ።
የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ በኤፍራታ ባለችው ለኤዝሪ አባት ለኢዮአስ በነበረችው ዛፍ በታች ተቀመጠ፤ ልጁም ጌዴዎን ከምድያማውያን ለማሸሽ በወይን መጭመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር።