እነሆ፥ ዛሬ ባሪያዎች ነን፤ ፍሬዋንና በረከቷን ይበሉ ዘንድ ለአባቶቻችን በሰጠሃት ምድር እነሆ፥ በእርስዋ ባሪያዎች ነን፥
ሰቈቃወ 5:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃችንን በገንዘብ ጠጣን፤ እንጨታችን በዋጋ በትከሻችን ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለምንጠጣው ውሃ መክፈል ነበረብን፤ ዕንጨታችንንም የምናገኘው በግዢ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውኃችንን በብር ጠጣን እንጨታችንን በዋጋ ገዛን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለምንጠጣው ውሃ ዋጋ እንከፍልበታለን፤ የማገዶ እንጨት እንኳ በዋጋ መግዛት አለብን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውኃችንን በብር ጠጣን እንጨታችንን በዋጋ ገዛን። |
እነሆ፥ ዛሬ ባሪያዎች ነን፤ ፍሬዋንና በረከቷን ይበሉ ዘንድ ለአባቶቻችን በሰጠሃት ምድር እነሆ፥ በእርስዋ ባሪያዎች ነን፥
እነሆ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ኀይለኛውን ወንድና ኀይለኛዋን ሴት፥ የእንጃራን ኀይል ሁሉ፥ የውኃውንም ኀይል ሁሉ ያስወግዳል፤
እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ሂዱ፤ ገንዘብም የሌላችሁ ሂዱና ግዙ፤ ብሉ፤ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ጠጡ።
በራብና በጥማት፥ በዕራቁትነትም፥ ሁሉንም በማጣት እግዚአብሔር ለሚልክብህ ለጠላቶችህ ትገዛለህ፤ እስኪያጠፋህም ድረስ በአንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭናል።