ሰቈቃወ 3:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርሃን ወደሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፊቱ አስወጣኝ፤ በብርሃን ሳይሆን በጨለማ እንድሄድ አደረገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርሃን ወደሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም ብርሃን ወደሌለበት ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርሃን ወደ ሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። |
ስለዚህ ፍርድ ከእነርሱ ዘንድ ርቆአል፤ ጽድቅም አላገኛቸውም፤ ብርሃንን ሲጠባበቁ ብርሃናቸው ጨለማ ሆነባቸው፤ ብርሃንንም ሲጠባበቁ በጨለማ ሄዱ፤
ሳይጨልምባችሁ፥ ጨለማም ባለባቸው ተራሮች እግሮቻችሁ ሳይሰነካከሉ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፤ በዚያም የሞት ጥላ አለና በጨለማውም ውስጥ ያኖራችኋልና ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ።
አሌፍ። እግዚአብሔር በቍጣው መቅሠፍት የጽዮንን ሴት ልጅ ምንኛ አጠቈራት! የእስራኤልን ክብር ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፤ በቍጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።
ዕውር በጨለማ እንደሚዳብስ በቀትር ጊዜ ትዳብሳለህ፤ መንገድህም የቀና አይሆንም፤ በዘመንህም ሁሉ የተገፋህ፥ የተዘረፍህም ትሆናለህ፤ የሚረዳህም የለም።
መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።