መሳፍንት 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አባቱም ቤት ወደ ኤፍራታ ገባ፤ ሰባ የሆኑትን የይሩበኣልን ልጆች ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ገደላቸው፤ ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ነበርና ተረፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዖፍራ ወደሚገኘው ወደ አባቱ ቤት ሄደ፤ ሰባውን የይሩባኣልን ልጆች፣ ወንድሞቹንም በአንድ ድንጋይ ላይ ዐረዳቸው፤ የይሩባኣል የመጨረሻ ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ስለ ነበር አመለጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዖፍራ ወደሚገኘው ወደ አባቱ ቤት ሄደ፤ ሰባውን የይሩበኣልን ልጆች ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ዐረዳቸው፤ የይሩበኣል የመጨራሻ ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ስለ ነበር አመለጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ አባቱ ቤት ወደ ዖፍራም ሄዶ የጌዴዎን ልጆች የሆኑትን ሰባውን ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ዐረዳቸው፤ የጌዴዎን መጨረሻ ልጅ ኢዮአታም ግን ተደብቆ ስለ ነበር ከሞት ተረፈ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አባቱም ቤት ወደ ዖፍራ ሄደ፥ ሰባ የሆኑትን የይሩበኣልን ልጆች ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ አረዳቸው፥ ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ነበርና ተረፈ። |
ወደ ሰማርያም ገብቶ ለኤልያስ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል እስኪያጠፋው ድረስ በሰማርያ የቀረውን የአክአብን ሰው ገደለ።
ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ የሀገሩ ሰዎች የንጉሡን ልጆች ሰባውን ሰዎች ይዘው ገደሉአቸው፤ ራሳቸውንም በቅርጫት አድርገው ወደ እርሱ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ።
ኢዮራምም በአባቱ መንግሥት ላይ ተነሥቶ በጸና ጊዜ ወንድሞቹን ሁሉ፥ ሌሎችንም የእስራኤልን መሳፍንት በሰይፍ ገደለ።
ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።
የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ በኤፍራታ ባለችው ለኤዝሪ አባት ለኢዮአስ በነበረችው ዛፍ በታች ተቀመጠ፤ ልጁም ጌዴዎን ከምድያማውያን ለማሸሽ በወይን መጭመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር።
ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም እስከ ዛሬ ድረስ “የእግዚአብሔር ሰላም” ብሎ ጠራው። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለኤዝሪ አባት በሆነችው በኤፍራታ አለ።
እናንተም ዛሬ በአባቴ ቤት ተነሥታችኋል፤ ሰባ የሆኑትን ልጆቹንም በአንድ ድንጋይ ላይ ገድላችኋል፤ ወንድማችሁም ስለሆነ የዕቅብቱን ልጅ አቤሜሌክን በሰቂማ ሰዎች ላይ አንግሣችኋል፥
“ለሰቂማ ሰዎች ሁሉ፦ ሰባ የሆኑት የይሩበኣል ልጆች ሁሉ ቢገዙአችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገዛችሁ ምን ይሻላችኋል? ብላችሁ ንገሩአቸው፤ ደግሞም እኔ የአጥንታችሁ ፍላጭ፥ የሥጋችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ።”
የሰቂማም ሰዎች ሁሉ፥ የመሐሎንም ቤት ሁሉ ተሰበሰቡ፤ ሄደውም በሰቂማ በዐምዱ አጠገብ ባለው የወይራ ዛፍ በታች አቤሜሌክን አነገሡ።