Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 21:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ኢዮ​ራ​ምም በአ​ባቱ መን​ግ​ሥት ላይ ተነ​ሥቶ በጸና ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን መሳ​ፍ​ንት በሰ​ይፍ ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ኢዮራም በአባቱ መንግሥት ላይ ተደላድሎ ከተቀመጠ በኋላ፣ ወንድሞቹን በሙሉ ከጥቂት የእስራኤል አለቆች ጋራ በሰይፍ ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ኢዮራምም በአባቱ መንግሥት ላይ ሥልጣን ይዞ በጸና ጊዜ ወንድሞቹን ሁሉ ሌሎችንም የእስራኤልን መሳፍንት በሰይፍ ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ኢዮራም መንግሥቱን ካጠናከረ በኋላ ወንድሞቹን በሙሉ እንዲሁም አንዳንድ የእስራኤል ባለሥልጣኖችን ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ኢዮራምም በአባቱ መንግሥት ላይ ተነሥቶ በጸና ጊዜ ወንድሞቹን ሁሉ ሌሎችንም የእስራኤልን መሳፍንት በሰይፍ ገደለ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 21:4
10 Referencias Cruzadas  

ቃየ​ልም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን፥ “ና ወደ ሜዳ እን​ሂድ” አለው። በሜ​ዳም ሳሉ ቃየል በወ​ን​ድሙ በአ​ቤል ላይ ተነ​ሣ​በት፤ ገደ​ለ​ውም።


አሁ​ንም ነዪ፤ የል​ጅ​ሽን የሰ​ሎ​ሞ​ንን ነፍ​ስና የአ​ን​ቺን ነፍስ እን​ድ​ታ​ድኚ እመ​ክ​ር​ሻ​ለሁ።


በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ግን ሄደ​ሃ​ልና፥ የአ​ክ​ዓ​ብም ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ ይሁ​ዳ​ንና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን እን​ዲ​ያ​መ​ነ​ዝሩ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ከአ​ን​ተም የሚ​ሻ​ሉ​ትን የአ​ባ​ት​ህን ቤት ወን​ድ​ሞ​ች​ህን ገድ​ለ​ሃ​ልና፥


ወደ ይሁ​ዳም ወጡ፤ በረ​ቱ​ባ​ቸ​ውም፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንም፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም ወሰዱ፤ ከታ​ና​ሹም ልጅ ከአ​ካ​ዝ​ያስ በቀር ልጅ አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።


የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የይ​ሁ​ዳን ቤተ መን​ግ​ሥት ዘር ሁሉ አጠ​ፋች።


ኢዩም የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ይበ​ቀል ዘንድ የይ​ሁ​ዳን መሳ​ፍ​ን​ትና አካ​ዝ​ያ​ስን ያገ​ለ​ግሉ የነ​በ​ሩ​ትን የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ወን​ድ​ሞች አግ​ኝቶ ገደ​ላ​ቸው።


መን​ግ​ሥ​ትም በእጁ በጸ​ና​ለት ጊዜ ንጉ​ሡን አባ​ቱን የገ​ደ​ሉ​ትን ባሪ​ያ​ዎች ገደለ።


ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።


ወደ አባ​ቱም ቤት ወደ ኤፍ​ራታ ገባ፤ ሰባ የሆ​ኑ​ትን የይ​ሩ​በ​ኣ​ልን ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቹን በአ​ንድ ድን​ጋይ ላይ ገደ​ላ​ቸው፤ ትንሹ የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ ኢዮ​አ​ታም ግን ተሸ​ሽጎ ነበ​ርና ተረፈ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos