መሳፍንት 8:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከተማዪቱንም ሽማግሌዎችና አለቆች ያዘ፥ የምድረ በዳንም እሾህና ኩርንችት ወስዶ የሱኮትን ሰዎች ገረፋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌዴዎን የከተማዪቱን አለቆች ወሰደ፤ በምድረ በዳ እሾኽና አሜከላ በመቅጣት የሱኮትን ሰዎች ትምህርት ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌዴዎን የከተማይቱን አለቆች ወሰደ፤ በምድረ በዳ እሾኽና አሜኬላ በመቅጣት የሱኮትን ሰዎች ትምህርት ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እሾኽና አሜከላ ከበረሓ ወስዶ የሱኮትን መሪዎች ገረፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከተማይቱንም ሽማግሌዎች ያዘ፥ የምድረ በዳንም እሾህና ኵርንችት ወስዶ የሱኮትን ሰዎች ገረፋቸው። |
ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፥ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፥ አሁን ይሸበራሉ።
ጌዴዎንም ወደ ሱኮት አለቆች መጥቶ፥ “ለደከሙት ሰዎችህ እህል እንሰጥ ዘንድ የዛብሄልና የስልማና እጅ አሁን በእጅህ ነውን? ብላችሁ የተላገዳችሁብኝ፥ ዛብሄልና ስልማና እነሆ፥” አለ።
ጌዴዎንም፥ “እግዚአብሔር ዛብሄልንና ስልማናን በእጄ አሳልፎ ቢሰጠኝ እኔ በምድረ በዳ እሾህና በኩርንችት ሥጋችሁን እገርፋለሁ” አለ።