የሞዓብም ንጉሥ እንደ ገደሉአቸውና ድል እንደነሡአቸው ባየ ጊዜ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰባት መቶ ሰዎችን ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ወደ ኤዶምያስም ንጉሥ ያልፉ ዘንድ ሞከሩ፤ አልቻሉምም።
መሳፍንት 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛብሄልና ስልማናም ከሠራዊቶቻቸው ጋር በቀርቀር ነበሩ፤ ሰይፍ የሚመዝዙ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች ወድቀው ነበርና ከምሥራቅ ሰዎች ሠራዊት ሁሉ የቀሩ ዐሥራ አምስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ዛብሄልና ስልማና ዐሥራ ዐምስት ሺሕ ከሆነ ሰራዊታቸው ጋራ ቀርቀር በተባለ ስፍራ ነበሩ፤ ይህም ከምሥራቅ ሕዝቦች ከተውጣጣውና በጦር ሜዳ ከወደቀው መቶ ሃያ ሺሕ ሰይፍ ታጣቂ ሰራዊት የተረፈው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ዜባሕና ጻልሙና ዐሥራ አምስት ሺህ ከሆነ ሠራዊታቸው ጋር ቀርቀር በተባለ ስፍራ ነበሩ፤ ይህም ከምሥራቅ ሕዝቦች ከተውጣጣውና በጦር ሜዳ ከወደቀው መቶ ሃያ ሺህ ሰይፍ ታጣቂ ሠራዊት የተረፈው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዜባሕና ጻልሙናዕ ከምሥራቅ ሠራዊት ከተረፉት ዐሥራ አምስት ሺህ ወታደሮቻቸው ጋር በቃርቆር ነበሩ፤ አንድ መቶ ኻያ ሺህ መሣሪያ የታጠቁ ወንዶች አልቀው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛብሄልና ስልማናም ከሠራዊቶቻቸው ጋር በቀርቀር ነበሩ፥ ሰይፍ የሚመዝዙ መቶ ሀያ ሺህ ሰዎች ወድቀው ነበርና ከምሥራቅ ሰዎች ሠራዊት ሁሉ የቀሩ አሥራ አምስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ። |
የሞዓብም ንጉሥ እንደ ገደሉአቸውና ድል እንደነሡአቸው ባየ ጊዜ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰባት መቶ ሰዎችን ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ወደ ኤዶምያስም ንጉሥ ያልፉ ዘንድ ሞከሩ፤ አልቻሉምም።
የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔርን ትተው ነበርና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በአንድ ቀን ከይሁዳ ጽኑዓን የነበሩ መቶ ሃያ ሺህ ሰልፈኞችን ገደለ፤
የእስራኤል ልጆች ከወንድሞቻቸው ሦስት መቶ ሺህ ሴቶችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ማረኩ፤ እጅግም ምርኮ ከእነርሱ ወስደው ወደ ሰማርያ አገቡ።
የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድኖች ሆነው አገኙአቸው።
በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ በላያቸው የነበረው ቀንበር ተነሥቶአልና፥ በጫንቃቸው የነበረውንም፥ የአስጨናቂዎችንም በትር መልሶአልና።
በዚያም ቀን ከየከተማው የመጡ የብንያም ልጆች ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም ከገባዖን ሰዎች ሌላ ሃያ አምስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከገባዖንም ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቈጠሩ፤
ከብንያምም ልጆች ሌላ የእስራኤል ሰዎች አራት መቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተቈጠሩ፤ እነዚህም ሁሉ ሰልፈኞች ነበሩ።
ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ የሕዝቡ ሁሉ አለቆች ሰይፍ በሚመዝዙ፥ በቍጥርም አራት መቶ ሺህ እግረኞች በሆኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ።
በሁለተኛውም ቀን የብንያም ልጆች ሊገጥሙአቸው ከገባዖን ወጡ፤ ከእስራኤልም ልጆች ደግሞ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎችን በምድር ላይ ገደሉ፤ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ።
እግዚአብሔርም ብንያምን በእስራኤል ፊት ጣላቸው፤ በዚያም ቀን የእስራኤል ልጆች ከብንያም ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሰዎችን ገደሉ፤ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ።
እንስሶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው በብዛት እንደ አንበጣ ሆነው ይመጡባቸው ነበር፤ ለእነርሱና ለግመሎቻቸው ቍጥር አልነበራቸውም፤ ምድሪቱንም ያጠፏት ዘንድ ይመጡ ነበር።
ብዛታቸውም እንደ አንበጣ የሆነ ምድያማውያንና አማሌቃውያን የምሥራቅም ልጆች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት ቍጥር እንደሌለው በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበረ።
ጌዴዎንም በደረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕልምን ለባልንጀራው ሲያጫውት፥ “እነሆ፥ ሕልም አለምሁ፤ እነሆም፥ አንዲት የገብስ እንጎቻ ወደ ምድያም ሰፈር ተንከባልላ ወረደች፤ ወደ ድንኳኑም ደርሳ እስኪወድቅ ድረስ መታችው፤ ገለበጠችውም፤ ድንኳኑም ወደቀ” ይል ነበር።
ሦስቱንም መቶ ቀንደ መለከቶችን ነፉ፤ እግዚአብሔርም የሰውን ሁሉ ሰይፍ በባልንጀራዉና በሠራዊቱ ሁሉ ላይ አደረገ፤ ሠራዊቱም በጽሬራ በኩል እስከ ቤትሲጣ ጋራጋታ ድረስ በጣባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልሜሁላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ።
ጌዴዎንም በድንኳን የሚኖሩ ሰዎች ባሉበት መንገድ በኖቤትና በዮግቤል በምሥራቅ በኩል ወጣ፤ ሠራዊቱም ተዘልሎ ሳለ አጠፋቸው።