Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 20:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የብ​ን​ያም ልጆች ሊገ​ጥ​ሙ​አ​ቸው ከገ​ባ​ዖን ወጡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ደግሞ ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰዎ​ችን በም​ድር ላይ ገደሉ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በዚሁ ጊዜም ብንያማውያን፣ እስራኤላውያንን ሊወጉ ከጊብዓ ወጡ፤ እንደ ገናም በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ሰዎች ገደሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በዚሁ ጊዜም ብንያማውያን፥ እስራኤላውያንን ሊወጉ ከጊብዓ ወጡ፤ እንደገናም በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ገደሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እንዲሁም ብንያማውያን በሁለተኛው ቀን ከጊብዓ ወጡ፤ በዚህም ጊዜ ዐሥራ ስምንት ሺህ የሠለጠኑ የእስራኤላውያንን ወታደሮች ገደሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በሁለተኛውም ቀን ብንያም ከጊብዓ በእነርሱ ላይ ወጣ፥ ከእስራኤልም ልጆች ደግሞ አሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ገደሉ፥ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 20:25
11 Referencias Cruzadas  

አቤቱ ይህ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ገዛ ይህን ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም።”


“ብን​ያም ነጣቂ ተኵላ ነው፤ በጥ​ዋት ይበ​ላል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንም ምግ​ቡን በማታ ለሕ​ዝብ ይሰ​ጣል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማዳ​ኑን አሳየ። በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት ቃል ኪዳ​ኑን ገለጠ።


እስ​ራ​ኤል ከጊ​ብዓ ዘመን ጀምሮ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ቶ​አል፤ በዚ​ያም ጸን​ተ​ዋል፤ በጊ​ብዓ ላይ ጦር አይ​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ው​ምን? መጥ​ቶም የዐ​መፅ ልጆ​ችን ገሠ​ጻ​ቸው፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባለ​ጠ​ግ​ነት፥ ጥበ​ብና ዕው​ቀት እን​ዴት ጥልቅ ነው! ለመ​ን​ገ​ዱም ፍለጋ የለ​ውም፤ ፍር​ዱ​ንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም።


ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።


በእኔ ኀጢ​አት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ከጸና እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰው ላይ ቅጣ​ትን ቢያ​መጣ ይበ​ድ​ላ​ልን? አይ​በ​ድ​ልም፤ የም​ና​ገ​ረ​ው​ንም በሰው ልማድ እና​ገ​ራ​ለሁ።


የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ከገ​ባ​ዖን ወጡ፤ በዚ​ያም ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን በም​ድር ላይ ገደሉ።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ሊዋጉ ቀረቡ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወጥ​ተው ወደ ቤቴል መጡ፤ አለ​ቀ​ሱም፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​መጡ፤ በዚ​ያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረቡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos