መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ መጣ፤ እርሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ ውጣ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊትም ተቀበላቸው፤ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።
መሳፍንት 6:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌዴዎንንም የእግዚአብሔር መንፈስ አጸናው፤ እርሱም ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ አብዔዜርም በኋላው ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የእግዚአብሔር መንፈስ በጌዴዎን ላይ ወረደ፤ እርሱም መለከት ነፋ፤ አቢዔዝራውያን እንዲከተሉት ጠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የጌታ መንፈስ በጌዴዎን ላይ ወረደ፤ እርሱም መለከት ነፋ፤ አቢዔዝራውያን እንዲከተሉት ጠራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር መንፈስ በጌዴዎን ላይ ወረደ፤ የአቢዔዜር ጐሣ ሰዎች ሁሉ እንዲከተሉት እነርሱን ለመጥራት እምቢልታ ነፋ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መንፈስ በጌዴዎን ገባበት፥ እርሱም ቀንደ መለከቱን ነፋ፥ የአቢዔዝርም ሰዎች ተጠርተው በኋላው ተከተሉት። |
መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ መጣ፤ እርሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ ውጣ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊትም ተቀበላቸው፤ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።
ዳዊትም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሳኦልን ሊወጋ በመጣ ጊዜ ከምናሴ ወገን ሰዎች ወደ ዳዊት ከዱ፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን፥ “በራሳችን ላይ ጉዳት አድርጎ ወደ ጌታው ወደ ሳኦል ይመለሳል” ሲሉ ተማክረው ሰድደውታልና እርሱ አልረዳቸውም።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በካህኑ በኢዮአዳ ልጅ በአዛርያስ ላይ መጣ፤ እርሱም በሕዝቡ ፊት ቆመና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? መልካምም አይሆንላችሁም፤ እግዚአብሔርን ስለ ተዋችሁ እርሱ ትቶአችኋል” አላቸው።
ዕጣውም ለቀሩት ለምናሴ ልጆች በየወገኖቻቸው፥ ለኢያዜር ልጆች፥ ለቄሌዝ ልጆች፥ ለኢየዚኤል ልጆች፥ ለሴኬም ልጆች፥ ለሱማሪም ልጆች፥ ለኦፌር ልጆች ሆነ፤ ወንዶቹ በየወገኖቻቸው እነዚህ ናቸው።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስቀሎናም ወረደ፤ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ልብሳቸውንም ገፍፎ እንቆቅልሹን ለነገሩት ሰዎች ሰጠ። ሶምሶንም ተቈጣ፤ ወደ አባቱም ቤት ተመለሰ።
የአህያ መንጋጋ አጥንት ወደ ተባለ ቦታም ደረሰ፤ ፍልስጥኤማውያንም ደንፍተው ተቀበሉት፤ ወደ እርሱም ሮጡ። የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በክንዱም ያሉ እነዚያ ገመዶች በእሳት ላይ እንደ ተጣለ ገለባ ሆኑ፤ ማሰሪያውም ከክንዱ ተፈታ፤
የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፤ ለጦርነትም ወጣ፤ እግዚአብሔርም በወንዞች መካከል ያለች የሶርያ ንጉሥ ኩሳርሳቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩሳርሳቴም ላይ በረታች።
ከዚህም በኋላ ወደ እስራኤል ምድር በደረሰ ጊዜ በተራራማው በኤፍራም ሀገር ቀንደ መለከት ነፋ፤ የእስራኤልም ልጆች ከእርሱ ጋር ከተራራማው ሀገር ወረዱ፤ እርሱም በፊታቸው ሄደ።
የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ በኤፍራታ ባለችው ለኤዝሪ አባት ለኢዮአስ በነበረችው ዛፍ በታች ተቀመጠ፤ ልጁም ጌዴዎን ከምድያማውያን ለማሸሽ በወይን መጭመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር።
እርሱም፥ “እኔ ዛሬ እናንተ እንዳደረጋችሁት ምን አደረግሁ? የኤፍሬም ወይን ቃርሚያ ከአቢዔዜር ወይን መከር አይሻልምን?
የእግዚአብሔርም መንፈስ በአንተ ይወርዳል፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፤ እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትለወጣለህ።
ዮናታንም በኮረብታው የነበሩትን የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ያን ሰሙ፤ ሳኦልም፦ እስራኤል ይስሙ ብሎ በሀገሩ ሁሉ ቀንደ መለከት ነፋ።