መሳፍንት 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዱሮ ጀምሮ የታወቀ ያ የቂሶን ወንዝ፥ የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በርቺ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥንታዊው ወንዝ፣ የቂሶን ወንዝ፣ የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው፤ ነፍሴ ሆይ፤ በኀይል ገሥግሺ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዱሮ ጀምሮ የታወቀ ያ የቂሶን ወንዝ፥ የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በኃይል እርገጪ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቂሶን ጐርፍ ጠራረጋቸው፤ የጥንቱ የቂሶን ወንዝ በጐርፉ ወሰዳቸው፤ ነፍሴ ሆይ! በርቺ! ገሥግሺ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዱሮ ጀምሮ የታወቀ ያ የቂሶን ወንዝ፥ የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በኃይል እርገጪ። |
ኤልያስም ሕዝቡን፥ “የበዓልን ነቢያት ያዙ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳን የሚያመልጥ አይኑር፤” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየወጋ ጣላቸው።
እኔን ለማዳን ረዳትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አምላኬ ነው፤ አመሰግነውማለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ።
እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ ዕረፍትን ይሰጠናል፤ እህልም በመንኰራኵር ጭድም በጭቃ እንደሚበራይ እንዲሁ ሞዓብ ይረገጣል።
ሲሣራም ሰረገሎቹን ሁሉ፥ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች፥ ከእርሱም ጋር የነበሩትን ሕዝቡን ሁሉ ከአሕዛብ አሪሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበሰባቸው።
እኔም የኢያቢንን ሠራዊት አለቃ ሲሣራን፥ ሰረገሎቹንም፥ ሕዝቡንም ሁሉ ወደ አንተ ወደ ቂሶን ወንዝ እስባለሁ፤ በእጅህም አሳልፌ እሰጠዋለሁ።”