መሳፍንት 5:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ! በሕዝብ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፤ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሠረታቸው ከአማሌቅ የሆነ አንዳንዶች ከኤፍሬም መጡ፤ ብንያም አንተን ከተከተሉ ሰዎች ጋራ ነበር፤ የጦር አዛዦች ከማኪር፣ የሥልጣን በትር የያዙም ከዛብሎን ወረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ፥ በሕዝብህ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፥ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀድሞ ዐማሌቃውያን ይኖሩበት ከነበረው ከኤፍሬም ወታደሮች መጡ፤ ሌሎችም ከብንያም መጡ። ከማኪር መሪዎች፥ ከዛብሎንም በትረ መንግሥትን የሚይዙ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ፥ በሕዝብህ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፥ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ። |
የኤፍራታዊው የኤሎን ልጅ ለቦንም ሞተ፤ በተራራማውም በአማሌቃውያን ምድር በኤፍሬም ባለችው በኤፍራታ ተቀበረ።
ከዚህም በኋላ ወደ እስራኤል ምድር በደረሰ ጊዜ በተራራማው በኤፍራም ሀገር ቀንደ መለከት ነፋ፤ የእስራኤልም ልጆች ከእርሱ ጋር ከተራራማው ሀገር ወረዱ፤ እርሱም በፊታቸው ሄደ።
ዲቦራም ባርቅን፥ “እግዚአብሔር ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር በፊትህ ይሄዳል” አለችው። ባርቅም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ።