መሳፍንት 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሞዓብም ንጉሥ ለዔግሎም እጅ መንሻውን አቀረበ፤ ዔግሎምም እጅግ ወፍራም ሰው ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግብሩንም ወፍራም ለነበረው ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን አቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግብሩንም ወፍራም ለነበረው ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን አቀረበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያን በኋላ ሰውነቱ በጣም ወፍራም ለነበረው ለዔግሎን ግብሩን ይዞ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሞዓብም ንጉሥ ለዔግሎም ግብሩን አቀረበ፥ ዔግሎምም እጅግ ወፍራም ሰው ነበረ። |
“ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ብሎአችኋልና፥ ሐሤትንም አድርጋችኋልና፥ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ተቀናጥታችኋልና፥ እንደ ብርቱዎችም በሬዎች ቷጋላችሁና፤
በዚያም ወራት ከሞዓብ ዐሥር ሺህ የሚያህሉትን፥ ጐልማሶችና ጽኑዓን ሁሉ ገደሉ፤ ከእነርሱም አንድ ሰው እንኳ አላመለጠም።
በመሥዋዕቴ ላይና በዕጣኔ ላይ ስለ ምን በክፉ ዐይን ተመለከትህ? የእስራኤል ልጆች በፊቴ ከሚያቀርቡት መሥዋዕት ሁሉ በቀዳምያቱ ስለ አከበርሁህ ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ለምን መረጥህ?