መሳፍንት 13:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ልጁ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለአምላክ የተለየ ይሆናልና፤ እስራኤልንም ከፍልስጥኤማውያን እጅ መታደግ ይጀምራል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ልጁ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናልና፤ እስራኤልንም ከፍልስጥኤማውያን እጅ መታደግ ይጀምራል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርግጥ ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን የራስ ጠጒሩን ፈጽሞ አይላጭ፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፥ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል። |
ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፤ አዋረዳቸውም፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ጌትንና መንደሮችዋን ወሰደ።
ከወንድ ልጆቻችሁም ነቢያትን፥ ከጐበዛዝቶቻችሁም ለእኔ የተለዩትን አስነሣሁ፤ እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ይህ እንደዚህ አይደለምን?” ይላል እግዚአብሔር።
“ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ ራሱን አይላጭ፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ ቅዱስ ይሆናል፤ የራሱንም ጠጕር ያሳድጋል።
እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል።
እርሱም፥ “ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር ናዝራዊ ነኝና ራሴን ምላጭ አልነካኝም፤ የራሴንም ጠጕር ብላጭ ኀይሌ ከእኔ ይነሣል፤ እደክማለሁም፤ እንደ ሌላም ሰው ሁሉ እሆናለሁ” ብሎ የልቡን ሁሉ ነገራት።
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።
እግዚአብሔርም ፍልስጥኤማውያንን አዋረዳቸው፤ ዳግመኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስራኤል ድንበር አልወጡም፤ በሳሙኤልም ዘመን ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ነበረች።