የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፤ ተቀበረችም።
መሳፍንት 11:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፦ ‘በምድርህ እንዳልፍ፥ እባክህ፥ ፍቀድልኝ’ ብሎ መልእክተኞችን ላከ፤ የኤዶምያስም ንጉሥ እንቢ አለ። እንዲሁም ወደ ሞዓብ ንጉሥ ላከ፤ እርሱም እንቢ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልም ወደ ኤዶም ንጉሥ፣ ‘በአገርህ እንዳልፍ እባክህ ፍቀድልኝ’ በማለት መልእክተኞችን ላከበት፤ የኤዶም ንጉሥ ግን አልሰማውም። ለሞዓብ ንጉሥም እንደዚሁ ላከበት፤ እርሱም አልተቀበለውም፤ ስለዚህ እስራኤል በቃዴስ ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም ወደ ኤዶም ንጉሥ፥ ‘በአገርህ እንዳልፍ እባክህ ፍቀድልኝ’ በማለት መልእክተኞችን ላከበት፤ የኤዶም ንጉሥ ግን አልሰማውም። ለሞዓብ ንጉሥም እንደዚሁ ላከበት፤ እርሱም አልተቀበለውም፤ ስለዚህ እስራኤል በቃዴስ ተቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ በምድሩ አልፈው እንዲሄዱ ይፈቅድላቸው ዘንድ ወደ ኤዶም ንጉሥ መልእክተኞች ላኩ፤ ነገር ግን የኤዶም ንጉሥ አልፈቀደላቸውም፤ የሞአብንም ንጉሥ እንዲሁ ጠየቁ፤ እርሱም ቢሆን በምድሩ አልፈው እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ ስለዚህ እስራኤላውያን በቃዴስ ቈዩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤል ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፦ በምድርህ እንዳልፍ፥ እባክህ፥ ፍቀድልኝ ብሎ መልክተኞችን ላከ፥ የኤዶምያስም ንጉሥ አልሰማም። እንዲሁም ወደ ሞዓብ ንጉሥ ላከ፥ እርሱም አልፈቀደም። |
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፤ ተቀበረችም።
በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች፥ በአሮዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በእግሬ ልለፍ።
የሞዓብም ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ ተነሥቶ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ፤ እንዲረግማችሁም የቢዖርን ልጅ በለዓምን ልኮ አስጠራው።