ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፥ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤
መሳፍንት 11:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮፍታሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ “ሀገሬን ለመውጋት ወደ እኔ የምትመጣ አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ?” ብሎ መልእክተኞችን ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዮፍታሔ ወደ አሞናውያን ንጉሥ፣ “ከእኔ ጋራ ምን ጠብ ቢኖርህ ነው መጥተህ አገሬን የወጋኸው?” በማለት መልእክተኞች ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዮፍታሔ ወደ አሞናውያን ንጉሥ፥ “ከእኔ ጋር ምን ጠብ ቢኖርህ ነው መጥተህ አገሬን የወጋኸው?” በማለት መልእክተኞች ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዮፍታሔ ወደ ዐሞን ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ “ከእኛ ጋር የተጣላህበት ምክንያት ምንድን ነው? አገራችንንስ የወረርከው ለምንድነው?” ብለው እንዲጠይቁት አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮፍታሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፦ አገሬን ለመውጋት ወደ እኔ የምትመጣ አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ብሎ መልክተኞችን ላከ። |
ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፥ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤
“ከቄድሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦
ዮፍታሔም ከገለዓድ ሽማግሌዎች ጋር ሄደ፤ ሕዝቡም መስፍን ይሆናቸው ዘንድ በላያቸው አለቃ አድርገው ሾሙት፤ ዮፍታሔም ቃሉን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በመሴፋ ተናገረ።
የአሞንም ልጆች ንጉሥ የዮፍታሔን መልእክተኞች፥ “እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ምድሬን ስለ ወሰደ ነው፤ አሁንም በሰላም መልሱልኝ” ብሎ መለሰላቸው።
ዮፍታሔም፥ “እኔና ሕዝቤ የተገፋን ነን፤ የአሞን ልጆችም በጽኑዕ አሠቃዩን፤ በጠራናችሁም ጊዜ ከእጃቸው አላዳናችሁንም።