ሠራዊትም በኀይል ይዘምቱባታልና፥ እንደ እንጨት ቈራጮችም በምሳር ይመጡባታልና ድምፅዋ እንደምትሸሽ እባብ ይተማል።
ኢያሱ 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆቹም “አዳንናችሁ፤ ለማኅበሩም እንጨት ትቈርጡና ውኃ ትቀዱ ዘንድ መደብናችሁ” አሉአቸው። አለቆቹም እንዲሁ አዘዙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ለማኅበረ ሰቡ በሙሉ ዕንጨት እየቈረጡ ውሃ እየቀዱ ይኑሩ።” ስለዚህ መሪዎቹ የገቡላቸው ቃል ተጠበቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቹም፦ “በሕይወት ይኑሩ” አሉአቸው፤ አለቆቹም እንደ ተናገሩአቸው ለማኅበሩ ሁሉ እንጨት ቆራጮች ውኃም ቀጂዎች ሆኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሪዎቹም ስለ እነርሱ በወሰኑት መሠረት፦ ይኑሩ፤ ነገር ግን ለመላው ማኅበር እንጨት በመልቀምና ውሃ በመቅዳት ያገልግሉ” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቹም፦ በሕይወት ይኑሩ አሉአቸው፥ አለቆቹም እንደ ተናገሩአቸው ለማኅበሩ ሁሉ እንጨት ቆራጮች ውኃም ቀጂዎች ሆኑ። |
ሠራዊትም በኀይል ይዘምቱባታልና፥ እንደ እንጨት ቈራጮችም በምሳር ይመጡባታልና ድምፅዋ እንደምትሸሽ እባብ ይተማል።
ሁላችሁ፥ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም፥ ሹሞቻችሁም፥ ጻፎቻችሁም፥ የእስራኤል ወንድ ሁሉ ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል።
እንዲህም ሆነ፤ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒቤዜቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ፥ ፈጽሞም እንዳጠፋት፥ በኢያሪኮና በንጉሥዋም ያደረገውን እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋም እንዳደረገ፥ የገባዖንም ሰዎች ከኢያሱና ከእስራኤል ጋር ሰላም እንዳደረጉ፥ በመካከላቸውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥
ኢያሱም ከእነርሱ ጋር ሰላም አደረገ፤ በሕይወት እንዲተዋቸውም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ የማኅበሩም አለቆች ማሉላቸው።
ስለማልንላቸው መሐላ ጥፋት እንዳይሆንብን ይህን አናድርግባቸው፤ በሕይወትም እንተዋቸው፤ እንግዛቸውም” አሉአቸው።
አሁንም የተረገማችሁ ሁኑ፤ ለእኔም፥ ለአምላኬም እንጨት ቈራጭ፥ ውኃም ቀጂ የሆነ ባሪያ ከእናንተ አይጠፋም” አላቸው።
በዚያም ቀን ኢያሱ እነርሱን ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቈራጮችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው። ስለዚህም የገባዖን ሰዎች ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ፥ እግዚአብሔርም ለመረጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ቈራጮች፥ ውኃም ቀጂዎች ሆኑ።