በዐሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎሞርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ረዐይትን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ከእነርሱም ጋር ጽኑዓን ሰዎችንና ኦሚዎስን በሴዊ ከተማ ገደሉአቸው፤
ኢያሱ 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞሬዎን ነገሥት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን፥ በአስታሮትና በኤድራይን በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ ባሉት በሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት ማለትም በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን፣ አስታሮትን ይገዛ በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ በነበሩት በሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል፤ እነዚህም ሁለቱ ነገሥታት በዐስታሮት ይኖሩ የነበሩት የሐሴቦን ንጉሥ ሲሖንና የባሳን ንጉሥ ዖግ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል። |
በዐሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎሞርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ረዐይትን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ከእነርሱም ጋር ጽኑዓን ሰዎችንና ኦሚዎስን በሴዊ ከተማ ገደሉአቸው፤
ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፥ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤
በሐሴቦን ተቀምጦ የነበረውን የአሞሬዎናውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስጣሮትና በኤድራይን ተቀምጦ የነበረውንም የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከገደሉት በኋላ፥
የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና፥ ልቡንም አጽንቶታልና።
በባሳንም ያሉት የዐግ መንግሥት ከተሞች፥ አስጣሮትና ኤድራይን ነበረ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፤ ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች እኩሌታም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት፥ እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።
ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፥ “እግዚአብሔር ምድሪቱን አሳልፎ እንደ ሰጣችሁ ዐወቅሁ፤ እግዚአብሔር እናንተን መፍራትን በላያችን አምጥትዋልና፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ የተነሣ ቀልጠዋልና።
ሽማግሌዎቻችንና የሀገራችን ሰዎች ሁሉ፦ ለመንገድ ስንቅ ያዙ፤ ልትገናኙአቸውም ሂዱ፦ እኛ ባሪያዎቻችሁ ነን፤ አሁንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ በሉአቸው አሉን።
እነርሱም አሉት፥ “በአምላክህ በእግዚአብሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪያዎችህ መጥተናል፤ ዝናውንም፥ በግብፃውያንም ያደረገውን ሁሉ፥