በበታችዋም፥ በዙሪያዋ በዐሥሩ ክንድ የበሬዎች ምስሎች ነበሩ። ኵሬዋንም ይከብቡአት ነበር። በሬዎቹም በሁለት ተራ ሁነው ከኵሬው ጋር በአንድነት ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ።
ኢያሱ 6:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም ተዋጊዎችን ሁሉ በዙሪያው አሰልፋቸው። ተዋጊዎቻችሁም ሁሉ በከተማዪቱ ዙሪያ አንድ ጊዜ ይዙሩ፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተማዪቱን ከተዋጊዎቻችሁ ጋራ አንድ ጊዜ ዙሩ፤ ይህንም ስድስት ቀን አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም ከተማይቱን ትዞሩአታላችሁ፥ ተዋጊዎቻችሁም ሁሉ ከተማይቱን በቀን አንድ ጊዜ ይዙሩአት፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተና ወታደሮችህ እስከ ስድስት ቀን ድረስ በቀን አንድ ጊዜ የከተማይቱን ቅጽር በሰልፍ ትዞሩአታላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰልፈኞቻችሁ ሁሉ ከተማይቱን አንድ ጊዜ ይዙሩአት፥ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ። |
በበታችዋም፥ በዙሪያዋ በዐሥሩ ክንድ የበሬዎች ምስሎች ነበሩ። ኵሬዋንም ይከብቡአት ነበር። በሬዎቹም በሁለት ተራ ሁነው ከኵሬው ጋር በአንድነት ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ።
ነገር ግን እናንተ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እኛ እናጠፋቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጊዜአቸው አልፎባቸዋል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው” ብለው ተናገሩአቸው።
ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።
ሕዝቡንም፥ “ሂዱ፤ ከተማዪቱንም ዙሩ፤ ተዋጊዎችም ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ ብላችሁ እዘዙአቸው” አላቸው።