የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊም እንዲህ አሉአቸው፥ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ለመስጠት ይህን ነገር እናደርግ ዘንድ አይቻለንም፤ ይህ ነውር ይሆንብናልና።
ኢያሱ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቻቸውን በእነርሱ ፋንታ አስነሣ፤ እነዚህንም ኢያሱ ገረዛቸው፤ በመንገድ ስለተወለዱ አልተገረዙም ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በእነርሱ ምትክ ወንዶች ልጆቻቸውን አስነሣ። እንግዲህ ኢያሱ የገረዛቸው እነዚህን ነበር፤ በጕዞ ላይ ሳሉ ባለመገረዛቸው ከነሸለፈታቸው ነበሩና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቻቸውን በእነርሱ ፋንታ አስነሣ፥ እነዚህንም ኢያሱ ገረዛቸው፤ በመንገድ ሳሉ ስላልገረዙአቸው ሸለፈታሞች ነበሩና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱ የገረዛቸው እግዚአብሔር በእነርሱ ቦታ ያስነሣቸውን ልጆቻቸውን ነው፤ እነርሱ በጉዞ ላይ በነበሩ ጊዜ ስላልተገረዙ ሸለፈታሞች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቻቸውን በእነርሱ ፋንታ አስነሣ፥ እነዚህንም ኢያሱ ገረዛቸው፥ በመንገድ ሳሉ ስላልገረዙአቸው ሸለፈታሞች ነበሩና። |
የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊም እንዲህ አሉአቸው፥ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ለመስጠት ይህን ነገር እናደርግ ዘንድ አይቻለንም፤ ይህ ነውር ይሆንብናልና።
ንጥቂያ ይሆናሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን እነርሱን አገባቸዋለሁ፤ እናንተም የናቃችኋትን ምድር ይወርሷታል።
ደግሞ፦ ይማረካሉ ያላችኋቸው ልጆቻችሁ፥ ዛሬም መልካሙን ከክፉ መለየት የማይችሉ ሕፃኖቻችሁ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ፤ ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ፤ ይወርሱአታልም።
እግዚአብሔርም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻችን የማለላቸውን ምድር እንደማያሳያቸው የማለባቸውን፥ ከግብፅ የወጡ የእግዚአብሔርንም ቃል ያልሰሙ፥ እነዚያ ተዋጊዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በመድበራ ምድረ በዳ ይዞሩ ነበር።