La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 5:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያሱ ሕዝ​ቡን ሁሉ የገ​ረ​ዘ​በት ምክ​ን​ያት ይህ ነው፤ ከግ​ብፅ የወጡ ወን​ዶች ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ ላይ በም​ድረ በዳ ሞቱ፤ የወ​ጡ​ትም ወን​ዶች ሁሉ ተገ​ር​ዘው ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንግዲህ ኢያሱ እስራኤላውያንን የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ዕድሜያቸው መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ከግብጽ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ ሳሉ በምድረ በዳ ሞቱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱ የገረዘበትም ምክንያት ይህ ነበር፤ ከግብጽ ከወጣው ሕዝብ መካከል ወንዶች ተዋጊዎች ሁሉ ከግብጽ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞተው ስለ ነበረ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢያሱ እነርሱን የገረዘበት ምክንያት ከግብጽ ምድር የወጡት ለወታደርነት ብቃት የነበራቸው ወንዶች ሁሉ በበረሓው ጒዞ ጊዜ ሞተው ስለ ነበረ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱ የገረዘበትም ምክንያት ይህ ነው፥ ከግብፅ የወጡት ሕዝብ ወንዶች ሰልፈኞች ሁሉ ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞቱ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 5:4
8 Referencias Cruzadas  

በግ​ብፅ ምድ​ርና በም​ድረ በዳ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴ​ንና ክብ​ሬን ያዩ እነ​ዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከእ​ነ​ርሱ በሁ​ሉም ደስ አላ​ለ​ውም፤ ብዙ​ዎቹ በም​ድረ በዳ ወድ​ቀ​ዋ​ልና።


የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ እስከ ተሻ​ገ​ር​ን​በት ድረስ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማለ​ባ​ቸው ተዋ​ጊ​ዎች የሆኑ የዚ​ያች ትው​ልድ ሰዎች ከሰ​ፈሩ መካ​ከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃ​ዴስ በርኔ የተ​ጓ​ዝ​ን​በት ዘመን ሠላሳ ስም​ንት ዓመት ሆነ።


“እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ተዋ​ጊ​ዎቹ ከጠፉ፥ ከሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ከሞቱ በኋላ፥


ኢያ​ሱም የባ​ል​ጩት መቍ​ረጫ ሠርቶ የግ​ር​ዛት ኮረ​ብታ በተ​ባለ ስፍራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ገረዘ።


ነገር ግን ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ፥ በም​ድረ በዳ የተ​ወ​ለዱ ሕዝብ ሁሉ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና፥ ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ገረ​ዛ​ቸው።