ሚስቱ ሲፓራም ባልጩት ወሰደች፤ የልጅዋንም ሸለፈት ገረዘች፤ “ይህ የልጄ የግርዛቱ ደም ስለ እርሱ ፈንታ ይሁን” ብላ ከእግሩ በታች ወደቀች።
ኢያሱ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ኢያሱን፥ “ከሻፎ ድንጋይ የባልጩት መቍረጫ ሠርተህ የእስራኤልን ልጆች ዳግመኛ ግረዛቸው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “የባልጩት መቍረጫ አዘጋጅተህ፣ ያልተገረዙትን እስራኤላውያንን ለሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም ጌታ ኢያሱን፦ “የባልጩት መቁረጫ ሠርተህ የእስራኤልን ልጆች ሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን “ከባልጩት የተሠራ መቊረጫ አዘጋጅተህ እስራኤላውያንን እንደገና ግረዛቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ኢያሱን፦ የባልጩት መቁረጫ ሠርተህ የእስራኤልን ልጆች ሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው አለው። |
ሚስቱ ሲፓራም ባልጩት ወሰደች፤ የልጅዋንም ሸለፈት ገረዘች፤ “ይህ የልጄ የግርዛቱ ደም ስለ እርሱ ፈንታ ይሁን” ብላ ከእግሩ በታች ወደቀች።
ዳሩ ግን አይሁዳዊነት በስውር ነው፤ መገዘርም በመንፈስ የልብ መገዘር እንጂ በኦሪት ሥርዐት አይደለም፤ ምስጋናውም ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።
ሳይገዘር እግዚአብሔር አብርሃምን በእምነት እንደ አጸደቀው በእርሱ ላይ ይታወቅ ዘንድ ግዝረትን የጽድቅ ማኅተም ትሆነው ዘንድ ምልክት አድርጎ ሰጠው። ሳይገዘሩ ለሚያምኑ ሁሉ አባት ሊሆን፥ አብርሃም በእምነት እንደ ከበረ እነርሱም በእምነት እንደሚከብሩ ያውቁ ዘንድ ሰጠው።
በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህን እግዚአብሔርንም በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ እንድትወድድ እግዚአብሔር ልብህን፥ የዘርህንም ልብ ያጠራዋል።
የኀጢአትን ሰውነት ሸለፈት በመግፈፍ በክርስቶስ መገረዝ በሰው እጅ የአልተደረገ መገረዝን በእርሱ ሆናችሁ ተገረዛችሁ።