La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 5:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ፤ ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ ምዕ​ራብ ፋሲ​ካን አደ​ረጉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤላውያን በኢያሪኮ ሜዳ በጌልገላ ሰፍረው ሳሉ፣ ወሩ በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የፋሲካን በዓል አከበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ ባለው ሜዳ በጌልገላ ሰፍረው ሳሉ፥ ከወሩ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የፋሲካን በዓል አከበሩ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፥ ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 5:10
14 Referencias Cruzadas  

እዩ፤ እኔም እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ወሬ እስ​ኪ​መ​ጣ​ልኝ ድረስ በም​ድረ በዳው ውስጥ በሜ​ዳው እቈ​ያ​ለሁ” አለው።


ወገ​ቦ​ቻ​ች​ሁን ታጥ​ቃ​ችሁ፥ ጫማ​ች​ሁን በእ​ግ​ራ​ችሁ ተጫ​ም​ታ​ችሁ፥ በት​ራ​ች​ሁ​ንም በእ​ጃ​ችሁ ይዛ​ችሁ እን​ዲህ ብሉት፦ እየ​ቸ​ኰ​ላ​ች​ሁም ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ፤ እርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ነውና።


ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን ሠርክ ጀም​ራ​ችሁ እስ​ከ​ዚሁ ወር ሃያ አን​ደኛ ቀን ሠርክ ድረስ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


በዚ​ህም ወር እስከ ዐሥራ አራ​ተኛ ቀን ድረስ ጠብ​ቁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሲመሽ ይረ​ዱት።


የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ተከ​ታ​ተ​ላ​ቸው፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም በኢ​ያ​ሪኮ ሜዳ አገ​ኙት፤ ይዘ​ውም በሐ​ማት ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ዴብ​ላታ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር አመ​ጡት፤ እር​ሱም ፍር​ድን በእ​ርሱ ላይ ተና​ገረ።


አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የስ​ደ​ተኛ እክት አዘ​ጋጅ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ቀን ለቀን ተማ​ረክ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ከስ​ፍራ ወደ ሌላ ስፍራ ተማ​ር​ከህ ሂድ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት እንደ ሆኑ ምን​አ​ል​ባት ያስ​ተ​ውሉ ይሆ​ናል።


“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን ሲመሽ የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔር ፋሲካ ነው።


ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።


ሕዝ​ቡም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወጡ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በም​ሥ​ራቅ በኩል በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ።


ከም​ድ​ሪ​ቱም ፍሬ ቂጣና አዲስ እህል በዚ​ያው ቀን በሉ።


ወደ ኢያ​ሱና ወደ እስ​ራ​ኤል ጉባኤ ወደ ጌል​ገላ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ “ከሩቅ ሀገር መጥ​ተ​ናል፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ” አሉ።


በየ​ዓ​መ​ቱም ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌል​ጌ​ላና ወደ መሴፋ ይዞር ነበር፤ በእ​ነ​ዚ​ያም በተ​ቀ​ደሱ ስፍ​ራ​ዎች ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር።