አንተ በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ የምድርም አሕዝብ ሁሉ ስምህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ይፈሩህ ዘንድ፥ በዚህም በሠራሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እንግዳው የሚለምንህን ሁሉ አድርግ።
ኢያሱ 4:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስክናልፍ ድረስ አምላካችን እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክንሻገር ድረስ አምላካችን እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችን አደረቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቀይ ባሕርን እንዳደረቀው ሁሉ፣ እናንተም እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ወንዝ በፊታችሁ አደረቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ ጌታ የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችን እግዚአብሔር እስክንሻገር ድረስ አስቀድሞ ለእኛ የቀይ ባሕርን እንዳደረቀልን፥ ለእናንተም የዮርዳኖስን ወንዝ እስክትሻገሩ ድረስ ውሃ አድርቆ ያሻገራችሁ መሆኑን ንገሩአቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ። |
አንተ በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ የምድርም አሕዝብ ሁሉ ስምህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ይፈሩህ ዘንድ፥ በዚህም በሠራሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እንግዳው የሚለምንህን ሁሉ አድርግ።
ከፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፤ በባሕሩም መካከል በደረቅ ዐለፉ፤ የተከተሉአቸውን ግን ድንጋይ በጥልቅ ውኃ እንዲጣል በቀላይ ውስጥ ጣልሃቸው።
እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማሪያህም በጎች፥ ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፤ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።
ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የአዜብ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፤ ባሕሩንም አደረቀው፤ ውኃውም ተከፈለ።
“የፈርዖን ፈረሶች ከሰረገሎቹና ከፈረሰኞቹ ጋር ወደ ባሕር ገቡ፤ እግዚአብሔርም የባሕሩን ውኆች መለሰባቸው፤ የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ መካከል በየብስ አለፉ፤ ውኃውም ለእነርሱ በቀኝ እንደ ግድግዳ፥ በግራም እንደ ግድግዳ ሆነላቸው።”